ቋንቋዬ ነሽ ድንግል | ዘማሪ ልዑልሰገድ ጌታቸዉ| ዝንተዓለም ኦርቶዶክስ |
Автор: ዝንተዓለም ኦርቶዶክስ Zinte Alem Orthodox
Загружено: 2022-04-06
Просмотров: 77774
Описание:
ዝንተዓለም ኦርቶዶክስ
ይህ ዩቲብ ገፅ ምንም አይነት ገንዘበብ የመስራት ፍላጎት የለዉም፡፡ ነገር ግን የኦርቶዶክስ መዝሙራት እና ስብከቶች ምዕመናን ጋር የደርስ ዘንድ ይተገጋል፡፡ እግዚአብሔር ሃሳባችንን ያሳካልን፤ ሁላችንንም እበርታ፡፡
ቤተክርስቲያን ላይ የሚደርስን ሁለገብ ተፅዕኖ መቃወም እና መከላከል አለብን፡
ቋንቋዬ ነሽ ድንግል መግባቢያዬ
መልስ የማገኝብሽ ከጌታዬ (2)
በአንቺ ቀርቤአለሁ ከአምላኬ ፊት
ቤቴ ሞልቶልኛል በበረከት(2)
አዝ...
በምን ስራዬ ነው ከፊቱ የቆምኩት
መቼ በቅቼ ነው ስሙን የጠራሁት
አስታራቂ እናት አንቺን ስለሰጠኝ
ስለ ቃልኪዳንሽ አቤት ልጄ አለኝ (2)
አዝ...
ቅድስና ሕይወት ከእኔ ተሰውሮ
በውሸት በሃሜት አንደበቴ ታስሮ
በእመ አምላክ ምልጃ አዲስ ሰው ሆኛለሁ
እንደ መላእክቱ ይኸው እዘምራለሁ (2)
አዝ...
ስለ እመ አምላክ ብሎ ያፈረ የለም
ባንቺ ያልከበረ ሰው አይገኝም
እንደ ባለማዕረግ እኔም ሰው መባሌ
አንቺን አግኝቼ ነው ድንግል መሰላሌ (2)
አዝ...
ሰላም ለኪ ብዬ ስጀምር ጸሎቴን
ሐሴት ይመለዋል መላው ሰውነቴን
እንደ ቅዱስ ኤፍሬም በምስጋናሽ ልጽና
በእጆችሽ ያለው አምላኬ ነውና (2)
አዝ...
ቋንቋዬ ነሽ ድንግል መግባቢያዬ
መልስ የማገኝብሽ ከጌታዬ (2)
ባንቺ ቀርቤአለሁ ከአምላኬ ፊት
ቤቴ ሞልቶልኛል በበረከት (2)
ዘማሪ ልዑልሰገድ
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: