ቅዱስ ዳዊት/ ዐረቦን ሚዲያ Arebon Media @ArebonMedia
Автор: ዐረቦን ሚዲያ Arebon Media
Загружено: 2026-01-15
Просмотров: 30
Описание: ከዛሬ ከሺዎች አመታት በፊት አንድ ይህ ቀረው የማይባል ሁሉ ነገር የተሟላለት ታላቅና ቅዱስ ሰው ነበር፤ እርሱም ፈጽሞ የጎደለው ነገር የሌለ በእግዚአብሔር ዘንድም ፍጹም የተለየ ስፍራ አለው፤ በጊዜውና በዘመኑ እጅግ በጣም የበዙ የጽድቅ ስራዎችን ሰርቷል የዛኑ ያህልም እርሱ ያደርጋቸዋል ተብለው የማይታሰቡ ከአዕምሮ በታች የሆኑ ታላላቅ ሀጢያቶች ፈጽሟል፤ ነገር ግን እንደ ሸረሪት ድር ከፊቱ ላይ የተተበተቡትን መሰናክሎች በእግዚአብሔር ሀይል ፍጹም አሸንፏቸዋል፤ ለዚህም ምስክር የሚሆነን ብዙ ዘመናትና አመታት አልፈው እንኳን በጥንቱ ዘመን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የፈጸማቸው ስራዎቹ ህያው ምስክር ናቸው።ይሄ ቅዱስና ታላቅ ሰው " የቅዱሳን ሀብታቸው ንሰሐቸው ነው " ለሚለው የቅዱሳን ብሒል ምስክር የሆነ ነው።ይህም ፊቱ እንደ ሮማን ቀይ ቁመቱም መካከለኛ አካሉም የጸና ብርቱ የሆነ፤ታናሽ ብላቴናም ሆኖ ሳለ እርሱ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ አንበሳ መጥቶ ከመንጋው ውስጥ በግ ነጥቆ በሚወስድ ጊዜ ተከትሎ ገድሎ ከአፉ ነጥቆ ያስጥለው የነበርው የመዝሙረኛው የቅዱስ ዳዊት ታሪክ ነው ፡፡
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: