ጠቃሚ እንቅስቃሴዎችና ዘዴዎች በሆድ ድርቀት ለምትሰቃዩ፣በዶ/ር ሳራ/Constipation exercises and relieving techniques Dr Sara
Автор: ዶክተር ሳራ / Doctor Sara
Загружено: 2024-05-02
Просмотров: 5464
Описание:
📌የሆድ ድርቀት የሚከሰተው ትልቁ አንጀት የተመገብነው ምግብ ብዙ ውሃ መጦ ሲያልቅ ነው፡፡ ይሁንና ድርቀትን የሚያመጡት የተለያዩ ምክንያቶች ናቸው፡፡
📌ለምሳሌ ያህል በፋይበር (አሰር) የበለጸጉ ምግቦችን ያለመመገብ፣ ዓይነ ምድር መጣሁ ሲል በወቅቱ አለመጸዳዳት፣ወተትና የወተት ተዋጾዎችን አዘውትሮ መመገብ፣እንቅስቃሴ አለማድረግ በተለይ በዕድሜ የገፉ ሰዎች፣እርግዝና እንዲሁም አንዳንድ እንደ ሳይኮትሮፒክ እና ናርኮቲክ ያሉ መድኃኒቶች ድርቀትን ሊመጡ ይችላሉ፡፡
📌የድርቀት ምልክቶች ከሆኑት ውስጥ የሆድ ሕመም፣የሆድ ጭብጠት፣የሆድ መንፋት፣ ማቅለሽለሽ እና የመግብ ፍላጎት ማጣት ናቸው፡፡ አብዛኛው ጤነኛ ሰው ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ አይነምድር ይወጣል፡፡ ዓይነ ምድር በውስጡ በቂ እርጥበት ያለው ከመሆኑም በላይ በሚወጣበት ጊዜ ያለአንዳች ስቃይ ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን ለሁለትና ከዚያ በላይ ቀናት መቆየት ዓይነ ምድር ያለመውጣት ችግርን ያመለክታል፡፡
📌አንንዳንድጊዜም የደረቀው ዓይነ ምድር ከታችኛው ትልቁ አንጀት ክፍል ተቀርቅሮ ለማስወጣት ስለሚያስቸግር በጣም ማማጥ ወይም መሰርሰር ባስ ሲልም አንጀትን መታጠብ አስፋላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ በዙ ማማጥ ግን የኪንታሮት በሽታ ሊያመጣ ይችላል፡፡
📌የሆድ ድርቀት ለመከላከል የሚረዱ ዘዴዎች
👉ውሃ መጠጣት፡- በሰውነታችን ውስጥ ያለው የውሃ መጠን ሲቀንስ የሆድ ድርቀት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለዚህ በቀን ውስጥ በቂ ውሃ መጠጣት የሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ ሴቶች በቀን ከ8-9 ብርጭቆ ውሃ እና ወንዶች ደግሞ በቀን ከ9-10 ብርጭቆ ውሃ ቢጠጡ ተብሎ ይመከራል፡፡
👉በፋይበር የበለፀጉ ምግቦች መመገብ፡- በምግቦች ውስጥ የሚገኝ ፋይበር የሚባል ቃጫ መሰል ንጥረ ነገር አለ፡፡ ፋይበር በሁለት ይከፈላል:-
1) ማይፈጭ ፋይበር፡- ሳይፈጭ በሰውነታችን ውስጥ የሚያልፍ ሲሆን ሰገራን የማለስለስ እና ከበድ እንዲል እና ከሰውነታችን ቶሎ እንዲወገድ የማድረግ ባህሪ አለው፡፡
2) የሚፈጭ ፋይበር፡- እንደዚህ አይነት ፋይበር በሚፈጭበት ጊዜ ከውሃ ጋር ይቀላቀላል እና ጄል ወደ ሚመስል ነገር ሰውነታችን ውስጥ ይቀየራል ይሄም ሰገራችን በቀላሉ እንዲወገድ ይረዳል፡፡
👉አፕል ወይም ፖም መመገብ፡-አፕል ውስጥ መፈጨት የማይችለው የፋይበር አይነት በብዛት ይገኛል፡፡ ይሄ አይነት ፋይበር ሰገራችን ቶሎ በሰውነታችን አልፎ እንዲወጣ ያግዘዋል፡፡ በተለይ አፕሉን ሳይላጥ መብላት ነው ያለብን፡፡
👉አሲድነት ያላቸው ፍራፍሬዎችና ውህዶች፡- ቆምጠጥ ያሉ ፍራፍሬዎች ማለት እንደ ብርቱካን፣ አናናስ ወይም ሎሚ፣አቼቶ ያሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ፍራፍሬዎችና ውህዶች በሁለቱም አይነት ፋይበር የበለፀጉ ስለሆነ የሆድ ድረቀትን ለማስታገስ ይጠቅማሉ፡፡
👉አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች፡- እንደ ሰፒናች፣ ብሮኮሊ የመሳሰሉት አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች ከፋይበር በተጨማሪ ቫይታሚን ኬ፣ ቫይታሚን ሲ እና ፎሌት የመሳሰሉትን ለጤናችን አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ይዘዋል፡፡
👉ስኳር ድንች፡- አንድ መካከለኛ የስኳር ድንች በውስጡ 3.8 ግራም የሚያህል ፋይበር ይይዛል፡፡ ስለዚህ የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ተመራጭ ምግብ ነው፡፡
👉ባቄላ፣ ምስር እና አተር፡- እነዚህ የማይፈጨውን እና የሚፈጨውን ፋይበር በብዛት ይዘዋል፡፡
👉የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
📌የቴሌግራም ቻነሌን ይቀላቀሉ👉https://t.me/healthtipsbydrsarayohannes
ስለሰውነት ክብደት መቀነስ/መጨመር👉 • የሰውነት ክብደት መጨመር ወይም መቀነስ የሚያስፈልገው መቼ ነው?Bo...
ስለቦርጭ መቀነሻ መንገዶች👉 • ያለእንቅስቃሴና ያለምግብ ለውጥ ቦርጭን ማጥፋት ይቻላል?በሳይንስ የ...
የመርሳት ችግር መፍትሄዎች👉 • የመርሳት ችግር ለገጠማችሁ/የማስታወስ ብቃት የሚጨምሩ ምግቦች በዶ/...
የቫይታሚን ዲ እጥረት👉 • የቫይታሚን ዲ እጥረት ምልክቶች | Vitamin D Deficiency...
የካንሰር መከላከያ መንገዶች👉 • ከ 30 እስከ 50% የሚሆነውን የካንሰር በሽታን በራሳችን መከላከል...
ኮሌስትሮል መቀነሻ መንገዶች👉 • የደም ውስጥ ኮሌስትሮል መጠን ከመጠን በላይ መጨመር የልብ ድካምን ...
በእርግዝና ጊዜ የሚደረጉ ጥንቃቄዎች👉 • ‼️በእርግዝና ወቅትመስተዋል ያለባቸው አደገኛ ምልክቶች ⚠️ dang...
#ethiopia #medical #ebs #helth #health #healthy #healthylifestyle #constipation #constipationhomeremedies #የሆድድርቀት #seifuonebs #seifufantahun #eshetumelese #etvnews #drsara #eritrea #intestine #guthealth #ድርቀት #family #familydoctor #familymedicine #doctor #youtube #youtuber #youtubevideo #youtubevideos #youtubeshorts #youtubeshort #youtubers #healthtips #google #tiktok #medicaleducation #public #love #exercise #water #food
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: