የዜማ ጊዜ | Apostolic Church | እልል በዪ | Apostolic song | Hossana Choir | የሆሳዕና መዘምራን
Автор: Iso Yisehak Ab
Загружено: 2023-02-22
Просмотров: 15958
Описание:
ከጥር 26-28/2015 በሆሳና በተካሄደው 51ኛው የሀድያ ሰበካ ጉባዔ ላይ የቀረበ የዝማሬ አምልኮ።
በእዚህ ጉባዔ 73 ሰዎች ወደ መዳን መጥተዋል ፣ 56 ሰዎች ከበሽታ ለመፈወሳቸው መስክረዋል ፣ ከ250 በላይ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በቅዱስ መንፈስ ተሞልተዋል።
ግጥም/Lyrics
ነጋ ለሊቱ ነጋ |4x|
ክረምት አለፈ የለቅሶ የዋይታ
የመከራ ዘመን በኢየሱስ ታለፈ
ማቅሽ ተቀደደ እንባሽም ታበሰ
የዜማ ጊዜ ይኸው ደረሰ
እልል እልል በዪ |3x|
ማቅሽን ቀዳድደሽ ተነሺ ዘምሪ
እልል እልል በዪ |3x|
ትቢያሽን አራግፈሽ ተነሺ ዘምሪ
1. በዓለት ንቃቃት ተሸሽገሽ ያለሽው
ውጪ ተገለጪ ዘመን መጣልሽ
የናቁሽ በሙሉ ወደ አንቺ ይመጣል
ከእግርሽ ስር ወድቀው ገና ይሰግዳሉ
ወይንሽም አብቧል ስዕለትሽም ሠምሯል
የመከራን ጊዜ በኢየሱስ አልፈሻል
ተነሺ ዘምሪ ዘመን መጥቶልሻል
የአማልክት አምላክ ድል አጎናጽፎሻል
እልል እልል...
2. ኃያላን ነገሥታት ዝናሽን ሰምተው ከሩቅ ይመጣሉ
ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ያዕቆብ አምላክ እንሂድ ይላሉ
ስፍራ ጠብቦናል የምናርፍበት
ኑ እንነሳ ለእግዚአብሔር ቤት ሥራ በአንድነት
ድንኳንሽን አስፊ ካስማዎችሽን ዘርጊ
ዓይኖችሽን አንስተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ
ከምስራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ
ከአራቱም አቅጣጫ ከዳር እስከዳር
ኢየሱስ በፉጨት ልጆቹን ይጠራል
ጽዮን ደስ ይበልሽ ዘመን መጥቶልሻል
ያለፈውን አታስቢ እንደ ክረምት አልፎ ሄዷል
አዲስ ነገር አዲስ ታሪክ ኢየሱስ በአንቺ ይሰራል |2x|
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: