የትምህርት ጤንነት መመርመሪያ፦ ክፍል 57 የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት
Автор: Evangelist Yared Tilahun
Загружено: 2026-02-23
Просмотров: 3916
Описание:
"አይሁድም፦ ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም፤ ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል። ከራሱ የሚናገር የራሱን ክብር ይፈልጋል፤ የላከውን ክብር የሚፈልግ ግን እርሱ እውነተኛ ነው በእርሱም ዓመፃ የለበትም።" ዮሐ. 7፡15-18
አይሁድ በጌታ ኢየሱስ ተዓምራት ከተደነቁት በላይ እነሱ በሚሉት መንገድ ሳይማር መጽሐፍትን በማወቁ ተደንቀዋል። ጌታ ኢየሱስ አድናቆቱን አልተቀበለም። "ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም" በማለት መለሰ። ወደ አባቱ ነው የጠቆመው። በዚህ ንግግር ውስጥ ጌታ ኢየሱስ አንድ ወሳኝ ነገር ተናግሯል። "ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል።" ትምህርት ከእግዚአብሔር ይሁን አይሁን የሚታወቀው በጭንቅላት ሳይሆን ፈቃዱን ለማድረግ አስቀድሞ በተዘጋጀ ልብ ነው። የትምህርትን ትክክለኝነት እና ስህተት የሚገልጥ እግዚአብሔር ነው። እሱ ደግሞ የሚገልጠው ለሁሉ ሳይሆን ምንም ይሁን ምን ለተገለጠው ፈቃዱ ለመታዘዝ የተዘጋጀ ልብ ላላቸው ነው። በሥጋ አእምሮ እና ጥበብ ስህተቱን ልንቀበል፣ እውነቱን ልንገፋ እንችላለን። ነገር ግን በምንም ሁኔታ ውስጥ ፈቃዱን ለማድረግ የጨከነ ልብ ሲኖረን ያኔ እግዚአብሔር ትምህርትን ይገልጥልናል።
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: