እጎላት እም እጎሊሆን አዲስ ኦርቶዶክስ መዝሙር፦ በመልአከ ገነት ዲበኩሉ በላይ
Автор: Kesis Dibekulu Belay Official
Загружено: 2019-10-02
Просмотров: 13026
Описание:
እጎላት እም እጎሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ፣
አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ ማርያም ድንግል(፪)
ተፈስሒ ፍስሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ፣
ከአንቺ ጋር ነውና አልፋና ዖሜጋ፣
ትፀንሲ ሲልሽ ቅዱስ ገብርኤል፣
ይኩነኒ ብለሽ ሥጋ ሆነ ቃል።
አዝ...
የአዳም ቃል ኪዳን በአንቺ ተፈጸመ፣
መልካም ዘር ሆነሽን መርገማችን ቆመ፣
ሙታን አይደለንም ሞት ተውጧል ዛሬ፣
ነፍስ አድኅን ሆኖልን የማሕጸንሽ ፍሬ።
አዝ...
ስለ ወለድሽልን የሚበላውን፣
ስላስገኘሽልን የሚጠጣውን፣
ሰለዚህ ድንግል ሆይ እንወድሻለን፣
ማርያም (፪) እያልን እንዘምራለን።
አዝ...
እጎላት እም እጎሊሆን አንቺን ይወዳሉ፣
ተሸክመውሻል ግራ ቀኝ ሳይሉ፣
ለሚያጠቧቸው ሳያዝኑ ሳይራሩ፣
ታቦተ ቃለ ጽድቅ እያሉ ዘመሩ።
አዝ...
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: