በዐቢይ ጾም ወቅት የሚሰገድ ሕይወትን የሚሰጥ አጋንንትን የሚደመስስ ታላቅ የአምልኮት ስግደት በተግባር በዲያቆን ሄኖክ ተፈራ።
Автор: Kesis Henok Tefera
Загружено: 2021-03-19
Просмотров: 90215
Описание:
በስመአብ ወወልድ ወመንፈሥ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
ጾምን ሊቀድስ ወደ ገዳመ ቆሮንጦስ ለገባ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
በገዳመ ቆሮንጦስ ለተራበ ለተጠማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
በገዳመ ቆሮንጦስ ከቆመ ሳይቀመጥ ለጸለየ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
በገዳመ ቆሮንጦስ ከዘረጋ ሳያጥፍ ለጸለየ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
በገዳመ ቆሮንጦስ 40 ቀንና ለሊት ለጾመ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
በገዳመ ቆሮንጦስ 40 ቀንና ለሊት ለጸለየ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
በገዳመ ቆሮንጦስ በዲያቢሎስ ለተፈተነ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
በገዳመ ቆሮንጦስ የዲያቢሎስን ፈተና ድል ለነሳ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
በገዳመ ቆሮንጦስ ዲያቢሎስን ላሸነፈ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
በገዳመ ቆሮንጦስ ለጾመ ለመለኮት ፍቅር እንሰግዳለን።
በገዳመ ቆሮንጦስ ለተራበ ለተጠማ ለመለኮት ፍቅር እንሰግዳለን።
ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
ለፈጣሪያችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
ለንጉሣችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
ለአዳኛችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
ለኃይላችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
ለአሸናፊያችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግዳለን።
ለመለኮታዊ ፍቅሩ እንሰግዳለን።
ለመለኮታዊ ትህትናው እንሰግዳለን።
ለመለኮታዊ አሸናፊነቱ እንሰግዳለን።
ለመለኮታዊ ምሕረቱ እንሰግዳለን።
ለመለኮታዊ ኃይሉ እንሰግዳለን።
ለመለኮታዊ ሰላሙ እንሰግዳለን።
ለመለኮታዊ ቸርነቱ እንሰግዳለን።
ለመለኮታዊ መድኃኒትነቱ እንሰግዳለን።
ለመለኮታዊ ሰውነቱ እንሰግዳለን።
ቅዱስ ለሆነው ለዐማኑኤል እንሰግዳለን።
ንጹሕ ለሆነው ለኢየሱስ እንሰግዳለን።
መሀሪ ለሆነው ለክርስቶስ እንሰግዳለን።
ቸር አዳኝ ለሆነው ለመድኃኔዓለም እንሰግዳለን።
አቤቱ ማረን
አቤቱ ይቅር በለን
አቤቱ በቸርነት ተመልከተን
አቤቱ ፈውሰን
አቤቱ አንጻን
አቤቱ ቀድሰን
አቤቱ ኃይልህን ላክልን።
ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና
አምልኮትና ውዳሴ ላንተ ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: