Tofik Yusuf - Yeznet Tela | ቶፊቅ ዩሱፍ - የእዝነት ጥላ (Official Music Video)
Автор: Tofik Yusuf
Загружено: 2024-10-11
Просмотров: 946909
Описание:
watch Tofik Yusuf - Yeznet Tela | ቶፊቅ ዩሱፍ - የእዝነት ጥላ(official Music Video)
connect with Tofik Yusuf:
Spotify : https://open.spotify.com/album/3a5zyR...
Tiktok: / tewfiq_yusuf
Instagram: / tofikyusufm
Official Youtube: / @tofikyusuf
Facebook: / tofikyusufm
Official Website: http://www.tofikyusuf.com
Credit:
Lyrics: Wubshet Shfraw
Melody: Wubshet Shfraw
Mixing & Mastering: Mohammed Raju
Special Thanks :
1. To Allah, the Lord of the worlds
2. To the owner of poetry and melody, Wubeshet Sheferaw
3. To my queen (Roza Mohammed Idris)
4. To the entire Seid family
5. To the youth groups of Nur Mosque
6. To Ustaz Bedru Hussein
7. To Aya Hotel
8. To Al-Bukhari Brand Collection
9. Acknowledging everyone who contributed to making this Nasheed clip possible
የእዝነት ጥላ *( Lyrics)
===========+=================
(ዜማ 1)
በዱንያ አክናፍ ብንሳፍፍ ዓለምን በጄ ባስገባ
ፀጋ ሞገሷን ደርቤ ምን ብዋብ በክብሯ ካባ
ሰውነኝና
የምድርን ፈተና ችየ ላፍታ አልኖርም አውቃለሁ
በብርታት በድክመቴ ውስጥ ከጎኔ አንተን እሻለሁ፡፡
( አዝማች)
አላሁ አ..አ አላሁ፣ያረሂሙ
ካንተ ውጭ አጋር የለኝ መጠጊያ
መዳኒቴ ነህ የልቤ መርጊያ
(ዜማ2)
ቅረበኝ ቅረበኝ ልበል ደስታየ ሞላ
ልከበብ ልጠለል ባ’ንተ የእዝነት ጥላ
ኒዕማህ ገብቶት በፍቅርህ ቀልቡ የራሰ
ሃሴቱ ልኬት የለውም ፀጋህን የተቋደሰ::
(ዜማ3)
እኔማ ምን አቅም አለኝ ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱ
ራህመትህ ሸፍኖኝ እንጂ ብመስል ለሰወች ብርቱ
እንከን ያልነካው ሃሴትን ላትቸረኝ ዱኒያ ደግ ሆና
መንገዴን አንተው አጽዳልኝ እንዳልስት ቅኑን ጎዳና
(ዜማ4)
ልቤም ትረጋጋለች =በፍቅርህ= ስላንተ ያሰበች ለታ
ይቀፈኝ የዝትህ ጸጋ ዘወትር ባንተ ልበርታ፡፡
ከቅጣት ይልቅ እዝነትህ =ቀዳሚ= ከበቀል መራጭ ይቅርታ
ሸኩር ነህ የኛማ ጌታ ለባሪያህ የምት ሰጥ ደስታ::
(አዝማች)
አላሁ አአ አላሁ፣ያረሂሙ
ካንተ ውጭ አጋር የለኝ መጠጊያ
መዳኒቴ ነህ የልቤ መርጊያ
(ዜማ2)
በፍቅርህ በፍቅርህ ልፍካ ባንተ ሁልጊዜ
በዝነትህ ፈውሰኝ ከልለኝ ከምድር ትካዜ
ላለማት እዝነት አድርገህ የኛን ሙሀመድ
ፍቅርህን ገልጸህልናል ባሪያህን እንደምትወድ፡፡
(ዜማ3)
ፀፀትን ተውባ አሸንፎት ወዳንተ የመጣን ለታ
ደጅህን የማትነሳን ከሩቁ ተቀባይ ጌታ፡፡
አምሳያ በሌለው ፍቅር፣ ስትቸረን ሞገስ ከግርማ
ቁጣህን ከኋላ አረካት እዝነትክን እንዳትሄድ ቀድማ፡፡
(ዜማ4)
በዚያ በጭንቁ ጊዜ=ወንጀሌ=በርክቶ ሚዛን ሲደፋ
መጠጊያ መሸሻም የለኝ አንተው ነህ ያለኸኝ ተስፋ
ሲያበራ የደጋጎች ፊት =ፀዳሉ= ስራቸው ባንተ ተወዶ
እኛንም ከነሱ አድርገን ብስራትህ ይድረሰን ማልዶ፡፡
(አዝማች)
አላሁ አአ አላሁ፣ያረሂሙ
ካንተ ውጭ አጋር የለኝ መጠጊያ
መዳኒቴ ነህ የልቤ መርጊያ(3...)
©️ Tofik Yusuf 2024
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: