ፅንስ ማስወረድ እና አደጋዎቹ
Автор: Yetena Kal HD የጤና ቃል
Загружено: 2020-09-16
Просмотров: 44185
Описание:
ፅንስ ማስወረድ ምንድን ነው?
ሴቶች ሳያስቡት ወይም ሳይወጥኑት ፅንስ ቢያስወርዳቸው የፅንስ መጨንገፍ ወይም ውርጃ ይባላል። ነገር ግን በፍላጎት ሆነ በእቅድ ፅንስን ለማስወገድ የሚደረግ ክንዋኔ ፅንስ ማስወረድ ይባላል።
ፅንስ ማስወረድ በተመለከተ የጤና ባለሙያዎች እና የሲቪል ማህበራት ያላቸው አስተያየት በሁለት ጎራ ይከፍላቸዋል።
በኣንድ በኩል
● ፅንስ ማቋረጥ የሴቷ መብት ነው። በመሆኑም ይህ መብት በህግም ሆነ በአገልግሎት አለማቅረብ ሳቢያ መገደብ የለበትም የሚል ሲሆን
በሌላ በኩል ደግሞ
● ፅንሱ ህይወት ያለው ፍጡር በመሆኑ ፅንስ ማስወረድ አውቆ እና ሆን ብሎ ህይወት እንደማጥፋት ይቆጠራል የሚሉ ወገኖች አሉ።
በአገራችን ያሉ ትላልቅ ሃይማኖቶችም ቢሆኑ ፅንስ ማስወረድን ይቃወማሉ።
በፅንስ ማስወረድ ሕጋዊ መሆን አለመሆን ያለው ውዝግብ በአገራችን ብቻ ሳይሆን በሁሉም አገሮች ውስጥ የሚካሄድ ነው። የዚህ ፅሁፍ አላማ ከአንደኛው ወይም ከሌላኛው ጋር መወገን ሳይሆን በፅንስ ማስወረድ ዙሪያ ያሉትን እውነታዎችና አደጋዎች ለማያውቁ ማሳወቅ ነው።
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: