"ከጥፋት አድነን"አዲስ የንስሐ መዝሙር በዘማሪ ታደሰ ጌታሁን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ኢዲቶሪያል ቦርድ ታይቶ የተፈቀደ።
Автор: ጳልቃን ሚዲያ PALKAN MEDIA ZEMARI TADESSE GETAHUN
Загружено: 2026-01-21
Просмотров: 847
Описание:
ከጥፋት አድነን
ልባችን ከመንገድህ ርቋል
ከነዓንን ትተን ካራን ተጉዘናል
ወደ ሕይወት መንገድ እንድንጓዝ ርዳን
በእናትህ ምልጃ ከጥፋት አድነን።
ትዕቢትን አርቀን ትሕትናንም ለብሰን
ምግባር እንድንሠራ ክፋትን አርቀን
ከጥፋት ጎዳና ጠብቅ ልጆችህን
ከቅዱሳን ጋራ በኅብረት አቁመን።
አገልጋዮችህን ላካቸው ወደ እኛ
ሕይወት እንድናገኝ እንዳንሆን ምንደኛ
ጠልፎ እንዳይወስደን ክፉ መልእክተኛ
እንድንሆን አድርገን የሰርጉ እድምተኛ።
አሮጌውን ጥለን ለብሰን አዲስ ልብስ
ለአንተ የሚገባ ለሰማይ ንጉሥ
በሥጋም በነፍስም በሚገባ ታጥበን
ከተመረጡት ጋር በቀኝህ አቁመን።
ፍሪዳውን አርደህ ወይኑን አዘጋጅተህ
ለመዳኑ ሕይወት ለክብሩ ጠርተህ
አንተ የጠራሃቸው እጅግ ብዙ ናቸው
የተመረጡት ግን ጥቂቶቹ ናቸው።
ለሕይወት ተጠርተው ወደ ሞት የሄዱት
እጅግ ብዙ ናቸው ካንተ የተለዩት
ወደ አንተ አቅርበን ለድኅነት አብቃን
በእሳት ከመቃጠል ከመጥፋት አድነን።
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: