🛑 በዓለ ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ የወረደበት | Ethiopian Orthodox
Автор: አክሊል ሚዲያ - Aklil Media
Загружено: 2025-06-07
Просмотров: 2920
Описание:
🛑 በዓለ ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ የወረደበት | Ethiopian Orthodox
✨✨✨ ጰራቅሊጦስ የሚለው የመንፈስ ቅዱስ ስም የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ መሆኑም ከማሳየት በላይ፤ ፍጹም አካል ያለው አምላክ እንደሆነ አመልካች ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጰራቅሊጦስ ማለት መሪ፣ አጽናኝ፣ ረጂ ማለት መሆኑን በስፋት ካስተማሩ ሊቃውንት በቀዳሚነት ይነሳል። ጰራቅሊጦሰ የተባለው መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። ሐዋርያዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ያላትን እምነቷን ስትገልጥ ‹‹ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ ዘሠረፀ እም አብ ንሰግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ››፤ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ ከአብ ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን፣ እናመሰግነዋለን፤›› የሚል ነው።
✨✨✨ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ፤ የቅድስናም ምንጭ ነው። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‹‹ወስመ መንፈስ ቅዱስ ነቅዐ ቅድሳትየ፤ የመንፈስ ቅዱስም ስም የቅድስናየ መገኛ ነው›› በማለት ገልጾታል።
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: