አከራካሪው ሪፖርት ሲጋለጥ! ያልተነገረው የኢትዮጵያ እውነተኛ የጦር አቅም! ከቁጥር በስተጀርባ ያለው እውነት! | Ethiopia and Egypt live
Автор: Gebeya Media - ገበያ
Загружено: 2026-02-08
Просмотров: 4284
Описание:
Related video፦ • ጨዋታ ቀያሪው ሱ-30 ጀት! ዓለምን ያስገረመው የኢትዮጵያ ወታደራዊ...
በዛሬው ልዩ ጥንቅራችን፦
በቅርቡ ይፋ የሆነው የግሎባል ፋየር ፓወር (GFP) የ2026 የዓለም የጦር ኃይሎች የጥንካሬ ደረጃ ግብፅን ከአፍሪካ ቀዳሚ፣ ኢትዮጵያን ደግሞ በአምስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧቸዋል።
ሪፖርቱ ኢትዮጵያ በምድር ጦር አቅሟ የአህጉሪቱ ቁንጮ መሆኗን ቢመሰክርም፤ አጠቃላይ የደረጃ አሰጣጡ ግን በወታደራዊ ሳይንስ ምሁራን ዘንድ ብርቱ ትችት እየቀረበበት ይገኛል። በዚህ ልዩ ጥንቀራችን የGFP ሪፖርትን ተዓማኒነትና መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር ያለውን ልዩነት በጥልቀት እንመረምራለን።
የተቋሙ መስፈርቶች ለጥራት ሳይሆን ለቁጥር ቅድሚያ የሚሰጡ በመሆናቸው፤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ ኃይሎችን አቅም ዝቅ አድርገው ሊያሳዩ እንደሚችሉ የዘርፉ ተንታኞች ስለመግለጻቸውም እንነግራችኋለን።
በተለይም እንደ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (Drones)፣ የኤሌክትሮኒክስ ጦርነትና የሳይበር ደህንነት ያሉ ወሳኝ የዘመኑ የጦር መሣሪያዎች በሪፖርቱ ውስጥ ያላቸው ቦታ አጠያያቂ ነው።
ከዚህም በላይ አንድን ጦርነት በድል ለመደምደም ወሳኝ የሆኑት እንደ የውጊያ ወኔ፣ የአመራር ብልሃት፣ የመልክዓ ምድር ልምድና የሕዝብ ደጀንነት ያሉ የማይዳሰሱ እሴቶች በGFP ሚዛን ላይ አለመቀመጣቸው የሪፖርቱን እውነተኛነት ጥያቄ ውስጥ ስለመክተቱ እናነሳለን።
በዚህም መሠረት የኢትዮጵያንና የግብፅን እውነተኛ ወታደራዊ አቅም ከመጋረጃ በስተጀርባ ባለው እውነት እንመዝናለን።
እንደ SIPRI እና IISS Military Balance ያሉ ዓለም አቀፍ የጥናት ተቋማት መረጃዎችን በማጣቀስ፤ በወረቀት ላይ ካለው ቁጥር ባለፈ በተግባር የሚታየውን የኃይል ሚዛን እንፈትሻለን።
እንደአጠቃላይም የአፍሪካ ቀንድና የሰሜን አፍሪካ ወቅታዊ ወታደራዊ ሽኩቻ ወዴት ያመራል? እንዲሁም፤ እውነተኛው የኃያልነት መለኪያ በጀቱ ወይስ የጦር ሜዳው ጽናት? የሚለውን ጉዳይ በዝርዝር እንመለከታለን።
ይህን ወቅታዊ ልዩ ጥንቅር እስከ መጨረሻው በመከታተል፤ ለሌሎችም እንዲደርስ Like እና Share ያደርጉት ዘንድ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡
💬 ሀሳብና አስተያየታችሁን በኮሜንት መስጫው ላይ ያጋሩን!
ለተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
🔔 Subscribe: [ / @gebeyamedia ]
#gebeyamedia #ገበያሚዲያ #ethiopia #globalfirepower #EthiopianMilitary #EgyptianMilitary #MilitaryRankings2026 #AfricaMilitary #EthiopiaVsEgypt #geopolitics #defenseanalysis #ኢትዮጵያ #ግብፅ #መከላከያ #የአፍሪካ_የጦር_ደረጃ #ዜና #አባይ #ወቅታዊ
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: