ኢትዮ ቴሌኮም የሚዲያ ስነ-ምህዳሩን የሚያዘምን የ“ቴሌስትሪም” አገልግሎትና የመደበኛ ብሮድባንድ የራስ አገዝ ዲጂታል አሰራርን በይፋ አስጀመረ!
Автор: Ethio telecom
Загружено: 2026-02-21
Просмотров: 1613
Описание:
ኩባንያችን የሚዲያ ስነ-ምህዳሩን የሚያዘምን አዲስ የ“ቴሌስትሪም” አገልግሎትና የመደበኛ ብሮድባንድ (ዋይ ፋይ) አገልግሎትን የሚያዘምን “ንክኪ-አልባ ዲጂታል አሰራር” በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል፡፡
ቴሌስትሪም በኩባንያችን የፋይበርና የቴሌ ክላውድ መሰረተ ልማት የሚቀርብ በመሆኑ ተጠቃሚዎች እስከ 4K የሚደርስ የምስል ጥራት ያላቸውን ይዘቶች በማንኛውም የአየር ሁኔታ ያለ መቆራረጥ እንዲመለከቱ ያስችላል።
አገልግሎቱ ስማርት ያልሆኑ ቴሌቪዥኖችን ወደ ስማርትነት በመቀየር ዘመናዊ የስትሪሚንግ አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ፈር ቀዳጅ አገልግሎት ነው፡፡
ይህ ፕላትፎርም የሀገራችንን ባህል፣ እሴትና ስነ-ምግባር መሰረት ያደረጉ ይዘቶችን የሚያቀርብ ሲሆን፤ የወላጆች ቁጥጥር ሥርዓት መካተቱ አስተማማኝና ተመራጭ ያደርገዋል።
ቴሌስትሪም የሚዲያ ተቋማት ለሳተላይት ኪራይ የሚከፍሉትን የውጭ ምንዛሬ የሚያስቀር ሲሆን፤ ለፊልም ፕሮዲውሰሮች፣ ይዘት ፈጣሪዎች፣ ለትምህርት እና ለቢዝነስ ተቋማት አማራጭ ይፈጥራል፡፡
በተጨማሪም ኩባንያችን የመደበኛ ብሮድባንድ አገልግሎት በማዘመን “ንክኪ-አልባ” የደንበኞቻችንን ተሞክሮ በእጅጉ የሚያሻሽል የዲጂታል ሲስተም ተግባራዊ ተደርጓል።
ይህም ደንበኞች ካሉበት ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ ውስጥ በሚገኝ ሚኒ-መተግበሪያ አዲስ ዋይፋይ እንዲጠይቁ ወይም የብልሽት ምዝገባ እንዲያከናውኑ ያስችላል፡፡
ደንበኞቻችን የቴሌስትሪም አገልግሎትን በዘመን ገበያ ወይም በአገልግሎት ማዕከሎቻችን፤ የብሮድባንድ አገልግሎታችንን ለማግኘት በቴሌብር ሱፐርአፕ እንዲጠቀሙ እንጋብዛለን፡፡
ለበለጠ፡ https://bit.ly/ethiotelTV
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: