ycliper

Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
Скачать

Yeberhan Moged| የብርሃን ሞገድ| Ethiopian music| Tewodros Tsegaye

Автор: ReyotKin ርዕዮት ኪን

Загружено: 2025-05-20

Просмотров: 25131

Описание: #የብርሃንሞገድ
“ያጠገቤን እንባ ራርቶ ካላበሰ፣
ለዝያ ቀዬ ጥሪ ልቤ ካልመለሰ፣
አጥንት እየለየ መርጦ ካለቀሰ፣
ሰው መሆን አበቃ ሳይካብ ፈረሰ፡፡”
እንግዲህማ፣ የግል አልበም ብቻ ሳይሆን የግል ዘፋኝም ኖረን ማለት ነው?
በቀደመው እለት፣ #ሌሊቴንተርጉማት በሚል ርዕስ ዘፈን አጋርቼ፣ የዚህችን ድምጻዊት ማንነት የለየ/ችን የመጀመርያ ሰው እንደምሸልም ገልጬ ነበር፡፡ መልሱን ያገኘው የመጀመርያው ሰው Nebyou Demssie ነው፡፡ ሌሎችም ወዳጆች በትክክል አግኝታችሁታል፡፡ ሙዚቃው የAI toolን በመጠቀም የተሰራ ነው፡፡ ነብዩ በውስጥ አነጋግረኝና ሽልማትህን ውሰድ፡፡
ደግሞ ሌላ ዘፈን!
#የብርሃንሞገድ ነኝ የህሊና ፀሃይ፣
መለኮት የሰራኝ በሌሎች እንድታይ፣
እሞቃለሁ ብዙ አበራለሁ ገና፣
የነበርኩ ያለሁት ለሌሎች ነውና፡፡
በልዩ ልዩ መንገዶች “የሚተረኩ ሀሳቦች አሉኝ” ለሚል ሁሉ ጊዜው ጥሩ፣ ቴክኖሎጂውም መልካም ረዳት ነውና፣ በዘፈን ቢገለጽ እጅግ እመኘው የነበረውን ሀሳብ እንዲይዝ አድርጌ ያዘጋጀሁትን ሌላ ሙዚቃ ደግሞ ላጋራችሁ፡፡
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጥናት የጀመርኩት AIን ለተቀላጠፈ የሚድያ ስራ እንዴት ማዋል ይቻላል? ለሚለው ጥያቄዬ መልስ ለማግኘት ነው፡፡ ኋላ ግን የሀሰሳዬ አድማስ ሰፍቶ የAI ሙዚቃ ሰፈር እራሴን አገኘሁት፡፡
የቀደመውን #ሌሊቴንተርጉማት የተሰኘውንም ሆነ ይህንን #የብርሃንሞገድ ሙዚቃ ያዘጋጀሁበትን ሂደት ላጫውታችሁ፡፡ ቅንብር ሳይሆን ዝግጅት የሚለውን ቃል የመረጥኩት በምክንያት መሆኑን ልብ በሉልኝ፡፡
መቼም እንዲህ እኔ እንደገጠመኝ አይነት በተምኔታችሁ ሙዚቃ እና በመጫወት ክህሎታችሁ መካከል ያለው ርቀት በእጅጉ ሲሰፋ ችግር ነው፡፡ እኔ ለእራሴው ደስታ እና ከጊዜአዊ ድባቴ ለመውጣት ያህል አልፎ አልፎ በመጠኑ ከሙዚቃ መሳርያዎች ጋር መጨዋወት ብወድም፣ በሀሳቤ ያለው ሙዚቃ ከእጆቼ መጠነኛ ችሎታ አቅም በላይ ነው፡፡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ያደረገልኝ ታድያ፣ የልቤን ሙዚቃዊ ሀሳቦች ወደሚደመጡ ስራዎች እንድተረጉም የሰለጠኑ ሙዚቀኛ እጆች ያዋሰኝ መሆኑ ነው፡፡ እኔ ሳዘጋጅ፣ እርሱ በዝርዝር መመርያዎቼ መሰረት የመሻቴን ሙዚቃ አቀናበረ እንደማለት፡፡
ወደዝግጅት ሂደቱ ልመለስ፡፡ በነገራችን ላይ፣ ቅደም ተከተሉ የግድ አይደለም፡፡
1፣ መጀመርያ ስንኞቹን ጽፌ እና በቁጥርም በአዝማች ከፋፍዬ ከበርካታ ይህን መሰል ተግባር መስራት ከሚችሉ የAI መከወኛዎች ለመረጥኩት tool ሰጠሁ፡፡ በዚህ ወቅት፣ የተለያየ ጥንካሬ እና ድክመት ያላቸው ሙዚቃ ቀማሪ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መከወኛዎች tools በርካቶች ናቸው፡፡
ከዝያም፣
2፣ ከግጥሙ ሀሳብ ጋር ይስማማሉ ያልኳቸውን የሙዚቃ ዘውግ እና ባህርይ (Genre and style መረጥኩ፡፡
3፣ ስለዜማው አይነት እና ቅርጽ ማብራርያ አኖርኩ፡፡
4፣ ስልተምቱን (Rhythm ወሰንኩ፡፡
5፣ ቅኝቱን (scale) ለይቼ አመለከትኩ፡፡
6፣ ሜጀሩን ጠቀስኩ፡፡
7፣ እንዴት ያለ ህብረድምጽ (Harmony፣ cord progression፣ Baseline እና የምት ጥንካሬ እንዲኖረው እንደምሻ በዝርዝር አሰፈርኩ፡፡
ቀጥሎም፣
8፣ የዘፋኝ ጾታ፣ የድምጽ ቀለምና አዘፋፈን፣ የጀርባ አጃቢዎች (Back vocalists) ወዘተ የተመለከቱ ምርጫዎቼን ዘረዘርኩ፡፡
9፣ በቅንብሩ ውስጥ እንዲካተቱ ስለምፈልጋቸው የሙዚቃ መሳርያዎች፣ ማጊያጌጫዎች ornaments, እንዲሁም Instrumentation, አይነት እና መጠን ገለጽኩ፡፡
10፣ በሙዚቃው አጀማመር እና በየመካከሉ እንዲገቡ ስለምሻቸው መሸጋገርያዎች Intro and bridges ያሰብኩትን ከተብኩ፣ ሌላም ሌላም፡፡
11፣ ይህንን አድርጌም በቀዳሚዎቹ ስራዎች የጠበቅሁትን ውጤት ስላልሰጠኝ ያለመታከት መመርያዎቼን በማሻሻል፣ በመቀያየር፣ በመጨመር እና በመቀነስ እዚህኛው ሙዚቃ ላይ ለመድረስ ደግሜ ደጋግሜ መሞከር ነበረብኝ፡፡
ይህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሙዚቃ አቀማመር፣ በዘፈን ተስተጋብተው መንፈስን ሊያክሙ እና ሊያለመልሙ ሲገባቸው በድምጻውያኑ ስንፍና፣ የተሳሳተ የገበያ ስሌት ወይም ህዝብ ነክ ግንዛቤ፣ የመረዳት እና የማብላላት አቅም ማነስ ወይም ዳተኝነት ሳይገለጹየቀሩ ብዙ አበይት ፍሬነገሮች አሉ ብሎ ለሚያምን ትልቅ በረከት ነው እላለሁ፡፡ ምክንያት፣ ስንኞች ሰው ይሰራሉና ነው፡፡
እናማ፣ አለፍ አለፍ እያልን፣ ድምጻዊ ማነጋገር አልያም አቀናባሪ ደጅ መቆም ሳያስፈልገን፣ ስለAI ጊዜ ሰጥተን እያነበብን፣ ሙዚቃ ማዘጋጀታችንን እንቀጥላለና!
AI ይበልጥ ይስላልን አቦ!
“ለመኖሬ ትርጉም ሌላ ሰው የምሻ፣
እኔም ልብ አካሚ የሌሎች ወጌሻ፣
ሰው ሁሉ ዘመዴ እንደሰውነቱ፣
የብርሃን ሞገድ ነኝ የማልመሽ በከንቱ፡፡”
#EthiopianMusic #TewodrosTsegaye #የብርሃንሞገድ #ሰውመሆን #ሰውነት #ሙዚቃ #ቴዎድሮስ

Не удается загрузить Youtube-плеер. Проверьте блокировку Youtube в вашей сети.
Повторяем попытку...
Yeberhan Moged| የብርሃን ሞገድ| Ethiopian music| Tewodros Tsegaye

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио

Похожие видео

እፎይ #Efoye #EthiopianMusic ቴዎድሮስ ፀጋዬ #TewodrosTsegaye ፅፎ እንዳዘጋጀው

እፎይ #Efoye #EthiopianMusic ቴዎድሮስ ፀጋዬ #TewodrosTsegaye ፅፎ እንዳዘጋጀው

Джем – Yeberhan Moged| የብርሃን ሞገድ| Ethiopian music| Tewodros Tsegaye

Джем – Yeberhan Moged| የብርሃን ሞገድ| Ethiopian music| Tewodros Tsegaye

Dr. Fikre tolosa defending

Dr. Fikre tolosa defending "achire"

Dibekulu, Leli - Set Alamnim - ዲበኩሉ x ሌሊ-ሴት አላምንም

Dibekulu, Leli - Set Alamnim - ዲበኩሉ x ሌሊ-ሴት አላምንም

የማትበላ ወፍ__ደርብ ዘነበ __አሰፋ አባተ ( AI Cover song)

የማትበላ ወፍ__ደርብ ዘነበ __አሰፋ አባተ ( AI Cover song)

YEMa -  Postegnaw  - የማ - ፖስተኛው - New Ethiopian Music 2024 - (Official Audio)

YEMa - Postegnaw - የማ - ፖስተኛው - New Ethiopian Music 2024 - (Official Audio)

የወሎ ልጅ - ተሾመ ምትኩ #amharic #amharicmusic #ethiopianmusic

የወሎ ልጅ - ተሾመ ምትኩ #amharic #amharicmusic #ethiopianmusic

ናይፍቕሪ መአዛ: #EthiopianMusic አበበ አርአያ እንደገና

ናይፍቕሪ መአዛ: #EthiopianMusic አበበ አርአያ እንደገና

Dawit Tsige - ድማማ | Demama (Official Concert Music Video)

Dawit Tsige - ድማማ | Demama (Official Concert Music Video)

በቴዲ አፍሮ 'ማር እስከ ጧፍ' ዘፈን ሃሳብ አልስማማም!  ቴዎድሮስ ፀጋዬ

በቴዲ አፍሮ 'ማር እስከ ጧፍ' ዘፈን ሃሳብ አልስማማም! ቴዎድሮስ ፀጋዬ

Kinie Fiker ቅኔ ፍቅር| #EthiopianMusic #TewodrosTsegaye ቴዎድሮስ ፀጋዬ ፅፎ እንዳዘጋጀው

Kinie Fiker ቅኔ ፍቅር| #EthiopianMusic #TewodrosTsegaye ቴዎድሮስ ፀጋዬ ፅፎ እንዳዘጋጀው

Samrawit Azene - Aya Tiragnma - ሳምራዊት አዘነ - አያ ጥራኝማ - New Ethiopian music 2025 (Official Video)

Samrawit Azene - Aya Tiragnma - ሳምራዊት አዘነ - አያ ጥራኝማ - New Ethiopian music 2025 (Official Video)

ችሎትህ ፊት #ChilothFit | #EthiopianMusic ቴዎድሮስ ፀጋዬ #TewodrosTsegaye ፅፎ እንዳዘጋጀው

ችሎትህ ፊት #ChilothFit | #EthiopianMusic ቴዎድሮስ ፀጋዬ #TewodrosTsegaye ፅፎ እንዳዘጋጀው

Menelik wossenachew  Wushetenaw

Menelik wossenachew Wushetenaw

ዘሩባቤል ሞላ - ምንድነው ዝምታው Zerubabbel Molla - Mindinew Zimitaw #mindinewzimitaw |

ዘሩባቤል ሞላ - ምንድነው ዝምታው Zerubabbel Molla - Mindinew Zimitaw #mindinewzimitaw |

Ethiopian Music _ በከተማው _ Beketemawu _ ስምኦን ተክለወልድ / Simon T/wold _ Live Band Music🎵

Ethiopian Music _ በከተማው _ Beketemawu _ ስምኦን ተክለወልድ / Simon T/wold _ Live Band Music🎵

Gigi Shibabaw – EsekeMeche ( እስከመቼ ) | Ethiopian Lyric Video & Meaning  Description:

Gigi Shibabaw – EsekeMeche ( እስከመቼ ) | Ethiopian Lyric Video & Meaning Description:

Dawit Senbeta - Honebin Tizita | ሆነብን ትዝታ - New Ethiopian Music 2019 (Official Video)

Dawit Senbeta - Honebin Tizita | ሆነብን ትዝታ - New Ethiopian Music 2019 (Official Video)

Addis Legesse - Becha Ney Enji - | ብቻ ነይ እንጂ - ( Official Lyrics Video)

Addis Legesse - Becha Ney Enji - | ብቻ ነይ እንጂ - ( Official Lyrics Video)

የልብ ክረምት #YelibKremt| #EthiopianMusic ቴዎድሮስ ፀጋዬ #TewodrosTsegaye ፅፎ እንዳዘጋጀው

የልብ ክረምት #YelibKremt| #EthiopianMusic ቴዎድሮስ ፀጋዬ #TewodrosTsegaye ፅፎ እንዳዘጋጀው

© 2025 ycliper. Все права защищены.



  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности



Контакты для правообладателей: [email protected]