Zema for Christ - ዜማ ለክርስቶስ - Meskelihin Ayalehu | መስቀልህን አያለሁ - 2020/2012
Автор: Zema for Christ - Official
Загружено: 2020-08-29
Просмотров: 402170
Описание:
ይህ መዝሙር አይናችንን እና ትኩረታችንን በመስቀሉ ላይ ስለማድረግ ነው፡፡
This song is about putting our eyes and focus on the Cross!
አይኖቼን ከመስቀልህ አንስቼ.......የመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሀ መዘምራን
ለሰው አላወራም........ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ)
መስቀልህን አያለሁ .........ኬነሳ ቡላ
ዓይኖቼን ከመስቀልህ አንስቼ
ወዴት እሄዳለሁ ካንተ ርቄ (2)
የሕይወቴ ሰላም ሁሌ የሚፈልቅበት
ከጭንቀትም ሁሉ ልቤ የሚያርፍበት
ሐዘን ከኔ ርቆ ደስታን የማገኘው
ዓይኖቼን አንስቼ መስቀልህን ሳይ ነው
ዓይኔን የጣልኩበት ከመስቀልህ ሌላ
ዘለቄታ የሌለው ጠፊ ነው በኋላ
ዓለሙም ምኞቱም ሁሉም ያልፋልና
እርዳኝ የኔ ጌታ ባንተ እንድፀና
ዓይኖቼን ከመስቀልህ...
የሚያስጨንቀኝን ላንተው እነግራለሁ
ትካዜዬን ሁሉ ባንተ ላይ እጥላለሁ
የመድሐኒቴ አምላክ ተስፋ አደርግሀለሁ/2/
ሰላም እረፍት መታደስን የማገኝበት
ስብራቴም የሚጠገንበት
አይኖቼን ወዳንተ አነሳለሁ
መስቀልህን አያለሁ
ወዴት እሄዳለሁ ካንተ ርቄ
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: