ሰማይ ነው //SEMAY NEW// NUHAMIN TEFERI (MAMA) NEW PROTESTANT MEZMUR 2022
Автор: Nuhamin Teferi
Загружено: 2022-12-22
Просмотров: 158681
Описание:
LYRICS
ለዘላለሙ ህይወት ጥሪው ለኔም ደርሷል
ሊፈጽመው ኢየሱስ በቅርብ ይመለሳል
ሰማይ አድርጎታል ሀሳቤን ቀድሶ
አሮጌውን ጥሎ አዲሱን አልብሶ
ሀገሬ ሰማይ ነው
ሀገሬ እላይ ነው
ሀሳቤ ሰማይ ነው
ሀሳቤ እላይ ነው
ሚጠፋውን ነገር ሰብስቤ አላከማች
ለሚቀረው ኑሮ አልልም እላይ ታች
ያከማቸሁትን እዚው ትቼው ልሄድ
ከምድራዊው ነገር ስለምን ልዋደድ
ይልቅስ ለሰማይ ለዘለአለሙ
ብተጋ ብለፋ ቢበዛም ድካሙ
ለማይቆጨው ልሩጥ ሩጫዬን በትጋት
በክርስቶስ ኢየሱስ ላገኘሁት እርስት
ሀገሬ ሰማይ ነው
ሀገሬ እላይ ነው
ሀሳቤ ሰማይ ነው
ሀሳቤ እላይ ነው
ሇላ ለሚፈርሰው ተግቼ አላንጽም
በጊዜያዊው ሀሳብ አልጠላለፍም
አይኖቼ ይነሱ ከምድራዊው ነገር
እግዚአብሄር ርስቴ ነው በሰማዩ ሀገር
ደግሞም በመምጣቱ አለ የምናፍቀው
ክብሩን እስክካፈል እጅግ የምጓጓዉ
የተባረከውን ተስፋዬን እስካገኝ
ልቤን ሚያበረታ መንፈስ ቅዱስ አለኝ
ሀገሬ ሰማይ ነው
ሀገሬ እላይ ነው
ሀሳቤ ሰማይ ነው
ሀሳቤ እላይ ነው
ጌታ ይባርካቹ 🙌
#NUHAMIN_TEFERI
#gosple_song
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: