ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ!!
Автор: meri feleke
Загружено: 2021-03-24
Просмотров: 9339
Описание:
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ!! (ርዕስ ነው!!)
"ቦታችን በተለመደው ሰዓት እጠብቅሃለሁ:: አፈቅርሃለሁ!" የሚል መልዕክት ነው እንዲህ ያስቦረቀኝ!!
እሱ ጏዳ ቁርስ እያበሰለ የሚያማስለው የመጥበሻ ድምፅ ይሰማኛል:: ስልኩ መልእክት ሲቀበል ድምፅ አሰማ ያለወትሮዬ እጅ ጥሎኝ ስልኩን አነሳሁት::
አንደኛ የራሳቸው ቦታ አላቸው! እኔና እሱ የኛ የምንለው ቦታ ኖሮን አያውቅም!! ከቤታችን ውጪ
ሁለተኛ የተለመደ ሰዓት አላቸው:: እኔና እሱ ለምንም የተለመደም የተመደበም ሰዓት የለንም:: የልደት ቀኖቻችንን እንኳን እረስተነው አልፎ ... 'ለካ ትላንት ነበር' የምንባባልበት ጊዜ አለ::
ሶስተኛና ዋነኛው ታፈቅረዋለች::
ይሄ ሲሰላ ቀመሩ እሱም ከኔ በላይ ያፈቅራታል ማለት ነው!
ደስ ሲል .....
"ምን ተገኘ?" ይለኛል አስሬ የሰራልኝን ቁርስ እያጎረሰኝ
"ምነው?"
"በጣም ደስ ብሎሻል! ይሄን ፈገግታ ካየሁት የማላስታውሰውን ያህል የጊዜ ርዝመት ያህል ዘመን ሆኖ ነበርኮ!" አለኝ የተለመደ የተመጠነ ፈገግታውን እየፈገገ... ዝም አልኩ
እያመነዘርክብኝ እንደሆነ ሳውቅ ነው ደስ ያለኝ! ይባላል? አይባልማ!!
እያለ ይቀጥላል
ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች እንደምን ከረምን? ሰላማችሁ እንደሰማይ ከዋክብት እንደማይቆጠር የምድር አሸዋ እጅጉን የበዛ ይሁን!! ይህ ሁል ጊዜ ማክሰኞ አመሻሽ ወደእናንተ የሚቀርበው ከተለመደው የሀሙስ ፕሮግራማችን በተጨማሪ ከእናንተ ጋር የምንገናኝበት «ከገፅ ወደ ጆሮ» የተሰኘ የተለያዩ ሰዎች ፅሁፎችን የምንተርክበት ፕሮግራም ነው። እንግዲህ ዛሬም «ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ!» የተሰኘ አጭር ልብወለድ የመጀመሪያ ክፍል እንዲህ ውብ ተደርጎ ተሰናድቶ ወደእናንተ ይዘን መጥተናል።
ክፍል ሁለት ይቀጥላል
ከወደዳችሁት #like #subscribe #share #comment ማድረጋችሁን እንዳትረሱ!!
የበዛ ክብርና ነፍፍፍፍፍ ፍቅር ለእናንተ ይሁን!!
new amharic drama every thursday. amharic motivational drama.
new amharic narration every thuesday. tiraka
facebook page - / meri-feleke-. .
facebook / meri.feleke.9
telegram channel https://t.me/yemeri_terekoch
tiktok https://vm.tiktok.com/ZSqqrLAL/
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: