ycliper

Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
Скачать

ከብፁዕ አቡነ ሰላማ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ | Abune Selama | ortodox tewhdo sibket 2023 | EOTC

Автор: Mikha Denagil ምክሐ ደናግል

Загружено: 2023-10-06

Просмотров: 91843

Описание: አቡነ ሰላማ
የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ
ዜና ህይወቱ ለብፁዕ አቡነ ሰላማ (የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ)
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሥላሴ ገ/መድኀንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ ልዩ ስሙ በዓታ ለማርያም በተባለው ፲፱፴፬ ዓ/ም ተወለዱ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ ሀገራቸው ንባብና የቃል ትምህርት በሚገባ የተማሩ ሲሆን ለግብረ ዲቁና የሚገባውንም ትምህርት ከየኔታ ክነፈ
ርግብ ተምረዋል ፤ ዲቁና ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል።
ብፁዕነታቸው ለቤተክርስቲያንና ለመንፈሳዊ ዕውቀት ባላቸው ጥልቅ ፍቅር በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን የተማሩ ሲሆን
ዜማ፡- ከየኔታ ተክለ ማርቆስ ማየ አንበሳ ገዳም (ተንቤን)
ቅኔ፡- ከየኔታ ንጉሤ መነዌ ገዳም (ተንቤን)
ቅኔ፡- ከየኔታ አክሊሉ ደበጋ (ጐንደር)
• ትርጓሜ መጻሕፍት- ከየኔታ ኃ/ማርያም ቀረፃ ማርያም ከምትሀባል ገዳም
ቅኔና ትርጓሜ መጻሕፍት፡- እንድባ ጊዮርጊስ ከየኔታ ልሳነ ወርቅ (ጐጃም)
● ቅኔ፡- ከየኔታ ዲበኩሉ (ጐጃም) በሚገባ ከተማሩ በኋላ ለመምህር ነት በቅተዋል፡፡
ከዚህ በኋላ በጐጃም ክ/ሀገር በፈረስ ቤት ሚካኤል፣ በጅጋ ሚካ ኤል ወንበር ዘርግተው ለ፲፪ ዓመታት ቅኔ በማስተማር አያሌ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል፡
መዝገበ ቅዳሴ ከየኔታ ልዑል (ቦረራ ሚካኤል) ተምረዋል፤ በወ ቅቱ የጐጃም ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አሱነ ማርቆስ የቅስናና የምንኵስና መዐርግ ተቀብለዋል።
ብፁዕ አቡነ ሰላማ በ ፲፱፻፷፬ ዓ.ም ወደ አርሲ ክፍለ ሀገር በመሄድ በወቅቱ የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በነበሩት በብፁዕ አቡነ ሉቃስ መልካም ፈቃድ በሀገረ ስብከቱ በማስተማር፣ የአውራጃ ሰባኬ ወንጌል በመሆን፣ የወረዳ ሊቀ ካህናት በመ ሆን በተለያዩ የኃላፊነት ሥራዎች ተመድበው በመሥራት ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል፤ በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፍርተዋል፤ በዚሁ ሀገረ ስብከት ለ፳፪ ዓመታት በማስተማር ቆይተዋል፤ በዚህም ሰፊ ወቅት ብዙ ደቀ መዛሙርትን አውጥተው ለቤተ ክርስቲያን አበርክተዋል፡፡
ብፁዕነታቸው ከአርሲ ሀገረ ስብከት በ፲፱፻፹፮ ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ ውቅያኖስ በሆነው እውቀታቸውና በቅድስናቸው ቤተ ክርስቲያንንም ሆነ ምእመናንን እንደሚጠቅሙ በማሰብ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በቅዱሳን ፓትርያርኮች ፈቃድና ትእዛዝ እየተሾሙ፦-
⇨ በቡራዩ ፄዴንያ ማርያም፣
⇨ በመተሐራ መድኃኔ ዓለም፣
-በቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤልና ሳሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣
⇨ በሰዓሊተ ምሕረት፣
⇨ በደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት በአስተዳዳሪነት ተመድበው ለበር ካታ ዓመታት በማስተማር በሚያስመንነው ስብከታቸው ብዙ አማ ንያንን አበርክተዋል፤ ለምናኔም አብቅተዋል፤ በተሰጣቸው ሀብተ ፈውስ በጸሎታቸው አያሌ ሕሙማንን ፈውሰዋል፧ ሰበካ ጉባኤን አጠናክረዋልº ስብከተ ወንጌልን አስፋፍተዋል፧ በተለይም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቀ ሥልጣናት ሆነው ለ ዓመታት ያህል በአስተዳደሩበት ጊዜ ከፈጸሟቸው ተግባራት ዋና ዋናዎቹ ምእመናን በጣዕመ ስብከታቸውና በቅድስናቸው እየተማረኩ ለካቴድራሉ በሚያደርጉት የቦታና የገንዘብ ልግስና በርካታ የሆኑ የልማት ተግባራትን አከናውነዋል።
❖ በዚህም መሠረት በትምህርታቸው በጎ አድራጊዎችንና ምእመናንን በማስተባበር በካቴድራሉ ስም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትና ከፍተኛ ክሊኒክ አሠርተው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ አክ ሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተባርኮ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው፡፡
⇨ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለ፭ ዓመታት ካገለገሉ በኋላ በእን ጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም በአስተዳዳሪነት አገልግለዋል።
⇨ ብፁዕ አቡነ ሰላማ ሙሉ የቤተ ክርስቲያን ትምህርታቸውን አጠናቅቀው በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር በአብነት መምህርነታቸው በተለይም በቅኔ መምህርነታቸው በተለያዩ አህጉረ ስብከት ወንበር ዘርግተው በማስተማር እስከ ጵጵስና ደረጃ የደረሱ አያሌ ምሁራንን አፍርተው ለቤተ ክርስቲያን ያስረከቡ፣ በልዩ የስብከት ችሎታቸው የታወቁ ሰባክያነ ወንጌልን ያፈሩና አማንያንን ያበዙ፣ ቅድስናን ከሙያ ጋር አስተባብረው የያዙ፣ የቅዱሳኑ፣ የፍጹማኑ ረድኤት ያልተለያቸው፣ እንደ አባቶቻቸው ቅዱሳን ሐዋር ያት አጋንንትን የማስወጣትና ሌላውንም ደዌ ሁሉ የመፈወስ ሀብተ ፈውስ የተሰጣቸው፣ በጥላቸው ብቻ ሕሙማንን የሚፈ ውሱ፣ የበቁ (ፍጹም) አባት ነበሩ።
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸው ተውህቦ የተወሰነ አይደለም ሀብተ ጸጋቸው ብዙ ነው! ጣዕመ ስብከታቸው ካለ መጠገቡም በላይ በተመስጦ በአካለ ሥጋ ያሳርጋልI ቅኔያቸውም ልዩ ጣዕም አለው ከማር ከወተት ይጣ ፍጣል! ፈጣሪያቸውን ብቻ አይደ ለም የሚያከብሩት፣ ሲበዛ ሰው አክባሪ ናቸው‥ ምንም ይሁን ምን በአርአያ እግዚአብሔር የተፈጠረውን ትልቁንም ትንሹንም ሁሉ በአክብሮት የሚወዱ አባት ነበሩ።
በአጠቃላይ ብፁዕ አቡነ ሰላማ የቤተ ክርስቲያናችን ጸጋና በረከት ነበሩ።በዚህ ቅድስና ቸው፣ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሙሉ ችሎታቸው፣ በአብነት መምህርነታቸው በርካታ ምሁራንን በማፍራታቸውና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናቸው ባበረከቱት ሰፊ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው ተመዝነው ብቁና ፍጹም አባት ሆነው በመገኘታቸው ሐምሌ ፱ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም በተደረገው የጳጳሳት ምርጫ ከሌሎች ዕጩ ቆሞሳት ጋር ተወዳድረው የድምፅ ብልጫ ስለ አገኙ የአክሱምና ማዕከላዊ ዞን ሃገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ሆነው የተመደቡ ሲሆን ከታኅሣሥ ፱/ ፪ሺ፪ ዓ/ም ጀምሮ የሰሜን ምዕራብ ሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከትን ደርበው እየሰሩ እስከ ግንቦት ፳፰/፪ሺ፭ ዓ/ም ድረስ ሐዋርያዊ ተግባራቸውን ሲፈጽሙ ቆይተዋል።
ግንቦት ፳፰ /፪ሺ፭ ዓ/ም ከትግራይ ማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተዛውረው የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም እና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው በ ፪ሺ፮ ዓ/ም የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ለ፮ ዓመታት በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ከፍተኛ ሐዋርያዊ አገልግሎትን ፈጽመዋል።
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከህዳር ፳፻ ፲፪ዓ/ም ጀምሮ በድጋሚ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም እና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ኃላፊ ሆነው በበአታቸው በመወሰን ሲያገለግሉ ቆይተው ባደረባቸው ሕመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም ፲፰ቀን፳፻ ፲ወ፮ ዓ/ም ይህን ዓለም በዕረፍተ ሥጋ ተለይተው ወደ ሰማያዊው አባታቸው ተጉዘዋል። በረከታቸው ይደረሰን
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም ቴሌግራም ቻናል
Telegram https://t.me/Mikhadenagil
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም ኢንስታግራም
Instagram   / mikhadenagi.  .
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም የዩቱብ ቻናል
Youtube https://www.youtube.com/channel/UCIiC...
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም ቴሌግራም ቻናል
Telegram https://t.me/Mikhadenagil
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም ኢንስታግራም
Instagram   / mikhadenagi.  .
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም የዩቱብ ቻናል
Youtube https://www.youtube.com/channel/UCIiC...
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም
| sibket ethiopian orthodox film | ethiopian orthodox sibket new 2023 | mezmur orthodox ethiopia | ethiopian orthodox kidase full | Ethiopia & Ethiopian Ortodox Tewahdo chruch documentary
ሰልክ ቁጥር +251975424242

#MikhaDenagil #EOTC #Ethiopia #abuneselama #tewodros_yosef #ethiopia #tewodrosbelete
unauthorised use, distribution and re upload of this content is strictly prohibited
Copyright ©2023 Mikha Denagil
#Ethiopia #EOTC #Ethiopia&EthiopianOrtodoxTewahdochruch #amharicmovie #ethiopia

Не удается загрузить Youtube-плеер. Проверьте блокировку Youtube в вашей сети.
Повторяем попытку...
ከብፁዕ አቡነ ሰላማ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ | Abune Selama  | ortodox tewhdo sibket 2023 | EOTC

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио

Похожие видео

የኪዳን ጸሎት መቅደም ትርጓሜ በአቡነ ሰላማ | Abune Selama | kidan tirguwame | ortodox tewhdo sibket 2023 | EOTC

የኪዳን ጸሎት መቅደም ትርጓሜ በአቡነ ሰላማ | Abune Selama | kidan tirguwame | ortodox tewhdo sibket 2023 | EOTC

Podwodny dron wleciał do wnętrza Titanica — a nagranie jest przerażające!

Podwodny dron wleciał do wnętrza Titanica — a nagranie jest przerażające!

😯👉[በቅዳሴ ጊዜ ይሄን እንዳታደርጉ]🟢🟢👉ተጠንቀቁ ስህተት ናቸው ዶክተር መጋቤ ሐዲስ ቴዎድሮስ በለጠ

😯👉[በቅዳሴ ጊዜ ይሄን እንዳታደርጉ]🟢🟢👉ተጠንቀቁ ስህተት ናቸው ዶክተር መጋቤ ሐዲስ ቴዎድሮስ በለጠ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስትያን እናምናለን

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስትያን እናምናለን

ሰበር ዜና |Ethiopia News ዛሬ | Ethiopian Daily News 9 Feb  2026

ሰበር ዜና |Ethiopia News ዛሬ | Ethiopian Daily News 9 Feb 2026

Попытка свержения власти / Лавров обвинил президента

Попытка свержения власти / Лавров обвинил президента

የአቡነ ሐራ ድንግል ሙሉ ገድል Abune hara dengel | የቅዱሳን ታሪክ | ገድለ ቅዱሳን | @ancientethiopia

የአቡነ ሐራ ድንግል ሙሉ ገድል Abune hara dengel | የቅዱሳን ታሪክ | ገድለ ቅዱሳን | @ancientethiopia

🔴በፈተና ፅና መንፈሳዊ ድራማ @Hamerehiwetmedia19

🔴በፈተና ፅና መንፈሳዊ ድራማ @Hamerehiwetmedia19

🛑ልብ የሚነካ የሚለውጥ ድንቅ ትምህርት//ጸልዩ//ጹሙ//ጸሎት የከበዳችሁ እንዲህ አደርጉ//መምህር መንግስቱ ጥላሁን(የእናቴ ልጅ)@AklilMedia2

🛑ልብ የሚነካ የሚለውጥ ድንቅ ትምህርት//ጸልዩ//ጹሙ//ጸሎት የከበዳችሁ እንዲህ አደርጉ//መምህር መንግስቱ ጥላሁን(የእናቴ ልጅ)@AklilMedia2

"ነፍስ ስንት ናት?" ጸሎተኛው የፈውስ አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ Abune Selama on pawlosmerewa tube

አቡነ ሉቃስ ይናገራሉ ፤ ከቀደመው ውድቀት የአሁኑ ይከፋል ።

አቡነ ሉቃስ ይናገራሉ ፤ ከቀደመው ውድቀት የአሁኑ ይከፋል ።

አትጨነቁ ለምኑት ይሰጣቹሀል እጹብ ድንቅ ምክረ አበው ቀሊቀሊቃውንት ዕዝራ ሃዲስ

አትጨነቁ ለምኑት ይሰጣቹሀል እጹብ ድንቅ ምክረ አበው ቀሊቀሊቃውንት ዕዝራ ሃዲስ

ንስሓ ስገባ የረሳሁት ኃጢአት  እንዴት ሊሆን ነው

ንስሓ ስገባ የረሳሁት ኃጢአት እንዴት ሊሆን ነው

"ክብረ ተክለሃይማኖት"በመላከ ሰላም መ/ር ታዬ አብርሃም | sibket 2022 | EOTC | ethiopia | tewahdo | melake selam taye

በኦርጋን ብንዘምር ምን አለበት? ለሚሉ በታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ ተሰጥቶ የነበረው መልስ

በኦርጋን ብንዘምር ምን አለበት? ለሚሉ በታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ ተሰጥቶ የነበረው መልስ

ትልቅ ምስጢር ያዘለ የተተረጎመ የአቡነ ሽኖዳ የመዳን ስብከት #አቡነ ሽኖዳ

ትልቅ ምስጢር ያዘለ የተተረጎመ የአቡነ ሽኖዳ የመዳን ስብከት #አቡነ ሽኖዳ

የኢትዮጵያ የአለም ብርሃን ምስጢር ሲገለጥ የፖትርያርኩ ውግዘት ! #orthodox

የኢትዮጵያ የአለም ብርሃን ምስጢር ሲገለጥ የፖትርያርኩ ውግዘት ! #orthodox

ልዩ ዝማሬ በሚሊኒየም አዳራሽ || ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ || ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ @21media27

ልዩ ዝማሬ በሚሊኒየም አዳራሽ || ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ || ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ @21media27

🟢👉[ለ10 ደቂቃም ጴንጤ አልሆንም]🟢🟢👉ህዝቡን በሳቅ ገደሉት መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ

🟢👉[ለ10 ደቂቃም ጴንጤ አልሆንም]🟢🟢👉ህዝቡን በሳቅ ገደሉት መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ

አቡነ ዘካሪያስ በእምባ ስለ አቡነ ሰላማ የነገሩን ያልተሰሙ ታሪኮች | ሰሞኑን ያጣናቸው አቡነ ሰላማ ማን ናቸው? | Haleta tv

አቡነ ዘካሪያስ በእምባ ስለ አቡነ ሰላማ የነገሩን ያልተሰሙ ታሪኮች | ሰሞኑን ያጣናቸው አቡነ ሰላማ ማን ናቸው? | Haleta tv

© 2025 ycliper. Все права защищены.



  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности



Контакты для правообладателей: [email protected]