ደፋር ሁን
Автор: እንቁ ምክሮች - Enqu Mikroch
Загружено: 2026-02-17
Просмотров: 463
Описание:
ሰዎች ቢያደንቁህ፣ ቢወዱህ፣ ቢያበረታቱህ መልካም ነው፤ የጠበከውን ያክል ምላሽ ባታገኝ፣ ድጋፉ ባይኖር፣ ሽልማቱ ባይኖር፣ እገዛው ቢቀር እንኳን ለእራስህ ድጋፍና ብርታት መሆን ይኖርብሃል።
ለስሜትህ የምትጠነቀቅ፣ ከውድቀት እራስህን የምትጠብቅ ከሆንክ የጠለቀውን ትስስር ከእራስህ ጋር እንጂ ከውጫዊው ተፅዕኖ ጋር አታደርግም።
አዎ! እላፊ የምትጠብቃቸው ሰዎችም ሆኑ ውጫዊ ማበረታቻዎች የቀሩ እለት ልብህን ይሰብሩታል።
የሰዎችን ማረጋጋጫ እየጠበክ የእራስህን ህይወት በነፃነት መኖር አትችልም።
እያንዳንዱን እርምጃህን እያሳወክ፣ ግልፅ እያደረክ፣ ከሰዎችም ጥሩ ምላሽ እየጠበክ መጓዝ መንገድህን እንቅፋት ያበዛበታል።
ትኩረት ለመሳብ ብለህ እራስህን ለማስረዳት ጊዜ አታጥፋ፤ አንተን የሚፈልጉ ሰዎች ቀድሞውኑ ጠየካቸውም አልጠየካቸውም ወዳንተ መምጣታቸው አይቀርም።
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: