ሳይኮሎጂ በኢትዮጵያ መቼ ተጀመረ? የሳይኮሎጂስቶች ስራ ምንድን ነው? How Psychology began in Ethiopia? Roles of Psychologists
Автор: Psychology ሥነልቦና
Загружено: 2025-09-14
Просмотров: 164
Описание:
በዚህ ቪዲዮ የሥነልቦና ሳይንስ በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ተካትቶ መሰጠት የጀመረበትን ሂደት ፣ የዘርፉን ዕድገት እንዲሁም ለሰዎች ኑሮ ጤናማነት ፡ ኢትዮጵያውያን የሥነልቦና ባለሙያዎች እያደረጉ ያለውን ድርሻ እንመለከታለን።
ይህ የዩትዩብ ቻናል የሥነልቦና ሳይንስ ምንነት በጥልቀት ይዳሰስበታል። የሰው ልጅ የሥነልቦና ውቅር ምን እንደሚመስል ይቃኝበታል። የሥነልቦና ሳይንስ ጽንሰ ሐሳቦች በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ ያላቸው ትርጉም በሰፊው ይብራራበታል። የሰው ልጅን ስሜቶችና ባህርያት በጥልቀት ከማስገንዘብ አንስቶ የሥነልቦና ጤናን ፣ የሰዎች መስተጋብርን እንዲሁም የግለሰብና የማኅበረሰብ ሁለንተናዊ ደህንነትን በበጎ መልኩ እስከማሻሻል የሚደርስ ግብ ያላቸው ሐሳቦች ይንሸራሸሩበታል። #psychology
#psychologyfacts #historyofpsychology #ethiopia
ዝግጅቶቻችንን የምናቀርበው በዋናነት በአማርኛ ቋንቋ ቢሆንም አልፎ አልፎ እንግሊዝኛን ጨምሮ አንዳንድ ከሌሎች ቋንቋዎች የተወሰዱ ቃላትን የምንጠቀም ይሆናል። ለዚህም ምክንያቶቹ ለምናነሳቸው ጉዳዮች የአማርኛ አቻ ቃላት በማይገኝ ጊዜ (የሥነልቦና ሳይንስ የሚዳስሳቸው በርካታ ጽንሰ-ሐሳቦች ለአገራችን በአንጻራዊነት አድስ በመሆናቸው) አልያም በእኛ በዝግጅት አሰናጆቹ የቋንቋ እውቀት ውስንነት ሊሆን እንደሚችል እናሳውቃለን። አብራችሁን ስለምትሆኑ እናመሰግናለን።
___
ማሳሰቢያ፡-
በዚህ የዩትዩብ ቻናል የምናጋራቸው መልዕክቶች ለትምህርታዊ ዓላማ ብቻ የተዘጋጁ መሆናቸውን እያስገነዘብን ከጤና ባለሙያ ጋር የሚደረግን ምክክርና የጤና ምርመራ (diagnosis) የሚተኩ እንዳልሆኑ ለማሳሰብ እንወዳለን።
___
DISCLAIMER:
Contents in this channel are for educational purposes only and are not intended to serve as substitute for consultation with health care professionals.
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: