ycliper

Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
Скачать

የደሞዝ ጭማሪ ለመንግስት ሰራተኞች | New salary increment for civil cervants

Автор: HIVN tube - ጤና መረጃ

Загружено: 2024-08-08

Просмотров: 243972

Описание: የመንግሥት ሰራተኞች የደረጃ እድገት እና የእርከን ጭማሪ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ተፈቅዷል! - የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
#salary #ethiopia #civilservant

አዲሱ የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የሰራተኞች አዋጅ ሰራተኞች ተመዝነው በአፈጻጸማቸው የሚለዩበት እንደሆነ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ገለጹ።

አዋጁን በተዛባ መንገድ መረዳት አይገባም ያሉት ኮሚሽነሩ፤ አንድ ሰራተኛ ሁለት ጊዜ ተመዝኖ ውጤቱ ከመካከለኛ በታች ከሆነ ከስራው እንደሚሰናበትም ጠቁመዋል።

በዚህ ምዘና በቂ ውጤት ያመጡ ሰራተኞች ደግሞ የደረጃ እድገት እንዲሁም በየሁለት ዓመቱ የሚኖር የእርከን ጭማሪ እንዲያገኙ በአዋጁ ተደንግጓል ብለዋል።

የአዋጁ ዋና ዓላማ ሰራተኛን መቀነስ ሳይሆን ማብቃት ነው ያሉት መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር)፤ በምዘናው ደረጃ አሟልተው ብቁ የሆኑ፣ የተወሰነ ክፍተት ያለባቸው እና ሰፋ ያለ ክፍተት የታየባቸው ተለይተው ክፍተቶቹ በስልጠና እየተሟሉ ሶስቱም በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚቀጥሉ ናቸው ብለዋል።

የመንግሥት ሰራተኛው በስራው ተመጣጣኝ ገቢ አለማግኘቱ በኑሮው ላይ ጫና ፈጥሮበታል፤ አዋጁ ይህን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ነው ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፥ አዋጁ የብቃት ምዘናውን ያለፉና መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ በእርከንና በደረጃ ዕድገት እያገኙ የሚሄዱበትን አስገዳጅ አሰራር መደንገጉን ተናግረዋል።

አዋጁ የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎትን ለማሻሻልና ዲጅታል ሲቪል ሰርቪስን ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ሁሉም ብሄረሰብ የተማረ የሰው ኃይል አለው ተብሎ ስለሚታሰብ ብዝሃነትን መሰረት ያደረገ ፐብሊክ ሰርቪስ ለመገንባት መታሰቡን ተናግረዋል።

ሥራ ላይ ያለው የፌዴራል መንግሥት የሰራተኞች አዋጅ ፖሊሲን መሰረት አድርጎ የተቀረጸ አይደለም ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የመንግሥት አገልግሎትን መሰረታዊ በሆነ መልኩ ለመቀየር የሚያስችልም አልነበረም ብለዋል።

አሁን የተዘጋጀው አዋጅ ነጻና ገለልተኛ ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት፣ የሰራተኛውን ብቃት ለማረጋገጥ፣ ብዘሃነትና አካታችነትን በተገቢው መንገድ ለመምራት እንደሚረዳ መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

✔ወቅታዊ የስራ ቅጥር መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት ቻናላችንን ይከታተሉ::

😀🌐 t.me/addlist/IWOV6uABAi5lYTA0 

🖥    / @hivn  

📱 www.fb.com/healthinovation/

Не удается загрузить Youtube-плеер. Проверьте блокировку Youtube в вашей сети.
Повторяем попытку...
የደሞዝ ጭማሪ ለመንግስት ሰራተኞች | New salary increment for civil cervants

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио

Похожие видео

© 2025 ycliper. Все права защищены.



  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности



Контакты для правообладателей: [email protected]