🔴 ዘወረደ - ዓብይ ፆም " የዓብይ ፆም የመጀመሪያ ሳምንት " Zewerede - Abiy Tsom Ethiopian Orthodox
Загружено: 2026-02-15
Просмотров: 525
Описание:
🔴 ዘወረደ - ዓብይ ፆም " የዓብይ ፆም የመጀመሪያ ሳምንት " Zewerede - Abiy Tsom Ethiopian Orthodox
🗯️🗯️🗯️ዘወረደ - ዓብይ ፆም
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡ ዘወረደ ማለት ‹ከላይ የመጣ፣ የወረደ ማለት ነው፡፡ ይህም የአምላካችን ሰው መሆን ያመለክታል፡፡ ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም ካለው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በመነሣት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በዚህ ዕለት ምስባክ ‹‹አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት፤ የሰማይን ሥልጣን ያለው የሁሉ ጌታ እንደሆነም ምንም አላወቁም›› ብሎ ተናግሮ ነበር፡፡ ይህም ድርሰት በቤተ ክርስቲያናችን የጾም መጀመሪያ የሆነው ዕለተ ሰንበት ዋዜማ፣ መግቢያ (መሐትው) ሆኖ ከዋዜማ በፊት ምንጊዜም በየዓመቱ ይቆማል፤ ይዘመራል፤ ይመሰገናል ማለት ነው፡፡
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: