ድል አድራጊው አጤ ምኒልክ / Emperor Menelik the Victorious
Автор: Ethiopian Ecclesiastical, Opera & Classical Music
Загружено: 2026-02-09
Просмотров: 731
Описание:
This composition was produced for the occasion of the 130th Anniversary of the Victory of Adwa. 9th Feb. 2026. Please see below the lyrics:
ሥራህ ባለም ታሪክ ተመዝግቦልሀል
አውሮፖ አሜሪካ እንዴት ይረሳሀል።
እምዬ ምኒሊክ ያፍሪካ ድል ጮራ
ጠላት ይናደዳል ታሪክህ ሲወራ።
ምኒሊክ ባድዋ ትልቅ ሥራ ሰራ
የነፃነት ፋኖን ላፍሪካ አበራ
የነፃነት ፋኖን ላፍሪካ አበራ።
እምዬ ቢባልም ስለደግነቱ
ባገሩ ከመጡ ማን ይቆማል ፊቱ።
ጣልያን በ ብዙ ታንክ እሱ በጎራዴ
ሶስቴ መሸነፍ ግን ሞት አይደለም እንዴ።
በአምባላጌ ምድር ድባቅ ብትመታቸው
መቀሌ ላይ መጡ በሙሉ ትጥቃቸው።
ዳግም ቢሸነፉም ቢወድቁ ከጅህ
ምረህ ለቅሀቸው ደግ ንጉስ ነህ።
አንበገር ብለው ባድዋ ቢመጡ
እምሽክ አረካቸው ከምድርዋ ሳይወጡ።
ምናሉ ጣልያኖች ሲገቧ ገራቸው
አይቀጡ ቅጣት ገርፎ ሲልካቸው።
አውሮፖም ተማረ ከጣልያን ሽንፈት
እሳቱን ደሚፋጅ ከምኒሊክ ቤት።
የጣልያንን ቁስል አውሮፖ ተረድቶ
ሰው አይወጣም አሉ ምኒሊክ ቤት ገብቶ።
እምዬ ቢባልም ስለደግነቱ
ባገሩ ከመጡ ማን ይቆማል ፊቱ።
ጣልያን በ ብዙ ታንክ እሱ በጎራዴ
ሶስቴ መሸነፍ ግን ሞት አይደለም እንዴ።
የስልጣኔ አየር የነፃነት ጮራ
አያልቅም እምዬ ታሪክህ ቢወራ
የምኒሊክ ሀገር እናት ኢትዮጵያችን
ትልቅ ፍቅር አላት ላንተ ንጉሳችን።
ይኖራል ሲነገር ታሪክህ ሲወራ
ትረፍልን ነፍስህ ከቅዱሳን ጎራ።
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: