ycliper

Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
Скачать

ድንቅ ነው የሚሰግዱ ድንጋዮች ያሉበት ጅሩ ቅድስት አርሴማ

Автор: ልቦና ቲዩብ Libona Tube

Загружено: 2021-04-09

Просмотров: 35014

Описание: የሚሰግዱ ድንጋዮች ያሉበት ጅሩ ቅድስት አርሴማ ጉዞ

የጉዞ ማስታወሺያ ስለ ጅሩ ቅድስት አርሴማ

ወደ ጅሩ አርሴማ መሄድ ለምትፈልጉ ከአ/አ ከተነሳችሁ የተሻለው አማረጭ በእነዋሪ መኪና በመሳፈር ደብረ ብርሃን ሳይገባ በሱሉለታ መስመር በሙከጡር አድርጎ ሲሃ ደብር መውረድ ከደብረ-ብርሃን ከተነሳችሁ ደግሞ ለሚ በሚለው መኪና በመሳፈር ሲያደብር መውረድ ወይም ከደብረ-ብርሃን ደነባ በሚለው መኪና ተሰፍሮ በሁለተኛ መኪና ወደ ሲያደብር መሄድ ይቻላል፡፡
እኔ በሶስተኛው አማራጭ ስለነበር የተጓዝኩት አረፋፍጄ 11፡ 00 ሰዓት ላይ ሲያደብር ደረስኩ፡፡ እቃ በሚሸከሙ የአገሬው ትሁታን ልጆች አማካኝነት እቃዬን አስይዤ በነሱ መሪነት ጎዞ ወደ ታላቋደብር ቅድስት አረሴማ ዘጅሩ ተጀመረ፡፡
አንድ እናት አርሴማ ለመድረስ ለደካማ 45 ደቂቃ ወይም 1፡ 00 ሰዓት ይወስዳል ነገር ግን ለበረቱት 30 ደቂቃ በቂነው ብለውኝ ነበር፡፡ ነገር ግን የአዋሳው ወደጄ ረጋ ብለህ ከተጓዝክ
3፡00 ሰዓት ትፈጃለህ ብሎኝ ስለነበር ለጉዞ ስነሳ ሁለቱ ሃሳቦች ተጋጭተውብኝ ነበር፡፡ ነገር ግን በጉዞው ያረጋገጥኩት አዋሳው ወዳጄን አባበል እውነትነት ነበር፡፡
ክፍል አንድ
በሰዓቱ ሊዘንብ ይከጅል ስለ ነበረ እሩጫ በሚባል እርምጃ ሜዳውን ጨርሰን ሸለቆውን ለመጀመር 25 ደቂቃ ወሰደብን።
ክፍል ሁለት
ሸለቆው (ገደሉ) ልክ ከፎቅ በደረጃ መውረድ ያህል ነበር፡፡ ቁልቁለቱ ጉልበት ያብረከርካል ዝም ብሎ ወደ ታች መውረድ አሁንም መውረድ ብቻ ነበር፡፡
በተለይ መንገዱ አንድ አንድ ቦታ በሁለት እግር ብቻ መውረዱን ትጠራጠሩና የቀሩትን ሁለቱንም እግራችሁን ማለት እጃችሁን መጠቀም ግዴታ ይሆናል፡፡
ለነገሩ እኔ ገና ከመነሻው የአገሬውን ልጆች በትር ይዤ ስለ ነበር በለሶስት እግር ነበርኩ፡፡ሶስቱን ስጠራጠር ደግሞ አራተኛውን እየተጠቀምኩ ቁልቁለከቱን ገፋውት፡፡
በነገራችን ላይ የቁልቁለቱ ነገር ሲነሳ ሸንኮራ ዩሀንስን ደብረ ይሰበይ አቡነ ሀብተማሪያም ገደምን ያየ ትልቅ ቁልቁለት አይቻለው ብሎ የሚል ሰው ካለ ጅሩ አርሴማ መጥቶ ቢያይ እጁን በአፉ ይጭናል፡፡
እኛ መኪና ውስጥ 30 ደቂቃ ቢፈጅ ነው ያሉኝ የደነቧዋ እመቤት ስመለስ ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ስህተት እንደይሰሩ ሰዓት ልገዛላቸው በጉዞው ላይ ተመኝቼ ነበር። ሸለቆው አንድ ሙሉ ሰዓት ብቻውን ፈጅቶብን ቁልቁለቱን አገባደድነው፡፡
ክፍል ሶስት
ግማሽ ቁልቁለት እና ተዳፈት መሰል ሜዳማ መንገድ ለመጨረስ በተጨማሪ 30 ደቂቃ ወስዶብን በአጠቃላይ መንገድ ላይ አንዴ ከአረፍንበት ጭምር ጥሩ ተጓዥ በሚያሰኝ አከሄድ ከሁለት ሠዓት የእግር ጉዞ በኋላ ተምረኛዋ ደብረልዕልና ቅድስት አርሴማ ደብር ወደ አንድ ሰዓት ገደማ ደረስን፡፡
ልክ አርሴማ ስትደርሱ እግር አጥበው መዝግበው የማረፍያ ስፍራ ይሰጡዋችዋል፡፡ እኔ የደረሰኝ አደራሽ ተብሎ በተለምዶ ከሚጠራው የፀሎት ቦታ በረንዳው ላይ ነበር፡፡
ይህንን ሁሉ ገዳል ወርጄ በግምት ከሁለት መቶ ሰው በቦተው ላይ ስመለከት በጎዞው ተፈጠረው ድካም ልክ እንደ ጉም በኖ ጠፋ፡፡
በተሰጠኝ ቦታ አነጣጥፌ በቀድሞቹ መጪዎች በተደረገልኝ የትህትና አቀባበል እየተደሰትኩ ጎኔን ከመሬት ጋር ወደ ሶስት ሰዓት ገደማ አገነኘውት፡፡
ከተመለከትኩት እና ከአስደነቁኝ ነገሮች መሀከል እዛ ካለው ሰው ከአንድ ሶስተኛው የመንፈስ ችግር አለበት፡፡
አብዛኛው ደግሞ ዛር፤ ውቃቢ ፤ቃልቻ የሚባለው የሰይጣን አይነት ነው፡፡ በእርግጥ ሌሎችም ህመምተኞች ቢኖሩም እነዚህ ግን ቦታው ይልቃሉ፡፡
ከእነሱ መሀል ጥቂት የሚያስቸግሩም በለሰንሰላቶች ቢኖሩም አብዛኞቹ ግን ሰው ሳያስቸግሩ ወደ ገደልም እንግባ ሳይሉ የሚኖሩ መሆናቸውን ስታዩ የእግዚአብሔር ጠብቆት ምንያህል ከሰይጠን ክፋት በላይ መሆኑን ትረደላችሁ፡፡
እንደሁም የሚያመውን ሰው ምትለየዩት በፀሎት ሰዓት የሚሆነው ካያችሁ በሃላ ነው፡፡ እንደው ደህና መስላቹ ሲያጫውታችሁ ውልና በመሃከል ከት ብሎ ስቆ እኔ እኮ ሰይጣኑ ነኝ አሳ ወይም እሱ አይደለም ብሎ ሊስቅባችሁ ስለሚችል ጤነኛውን ከባለመንፈሱ ለመለየት ዋል አደር ማለት ይጠይቃል።
እዚህ ቦታ ከሚያስገርመው አንዱ ደግሞ ይህን ያህል ሰው እንዴት አንደመጣ ስታጣሩ ተልከው እንደመጡ ትሰማላችሁ፡፡ ከዬት ብትሉ ከፃድቀኔ ማርያም፤ ሽንቁሩ ሚከኤል፤ከመሳሰሉት የሚል ይሆናል፡፡
በነገራችን ላይ ከዚህ ተልከው ወደ ሌላ ቦታ የሚሄዱም አሉ፡፡ ለምሳሌ ወደ ታላቋ የወሎ ሲርንቃ አርሴማ ገዳም የተላኩና የወጡ ሰዎች በብዛት አይቻለው፡፡
እንዴት ነው መልዕክቱን የሚያገኙት ብትሉ?? በሁለት አይነት
መልኩ የሚለው መልስ ይሆናል ፡፡ ይህም ማለት አንዱ በራዕይ ሁለተኛው ደግሞ መንፈሱ ሲለፈልፍ መውጫውን ቦታ ስለሚጠቁም ነው። በነገራችን ላይ ይህ ነገር የሆስፒታሉን referral system አስታውሶኛል፡፡
አንዳንዶች እንደውም ሰማእቷ ከረዳችኝ መልሱን አገኛለሁ ካለሆነም referral ይጻፍልኛል ይላችኋል ፡፡አይገርምም ????
ሰማእቷ ቅድስት አርሴማ የምትታወቀው ዘንባባ በመያዟ ሲሆን ( በነገራችላይ ጽዋ የያዘችውን ስዕል በአብዛኛው በኢትዮጵያ የአርሴማ ሚባለው የቅድስት ባርባራ ስዕል መሆኑን እዚ ላይ ያጠይቅዋል ) ታዲያ በድብሩ ዙሪያ ያሉ ድንጋዮች ተፈንቅለው ሲከፈሉ የዘንባባ ምስል መገኘቱ የቦታውን ታምራተኛነትን ያረጋግጣል።
እንደሁም አንዳንዱ በቅጠል ቅርጽ ዘንባባውን እያስቀረጹ ፊቱን መስቀል በማድረግ በስተው ማንጠልጠል የተለመደ ሲሆን እኔም ለበረከት አንድ ሁለት ደርሶኛል በደበሯ ሁሉም ሰው የሚጠቀምበት አንድ ብዙ ሰው የሚያስተናግድ ሽንት ቤት ነበር፡፡
አሰራሩ በተራራ ጫፍ ላይ ስለነበር ከስራ ጥራቱ ጉድለትም በላይ ንፋስ የሚወዘውዘው በመሆኑ የሚያሰጋ ሽንት ቤት ነበር፡፡በቀን 1/13/2003
በማታ የአንድ ሰአት ጸሎት ላይ ፤ሁሉም ምህላ ገብቶ በነበረ ጊዜ የተወሰኑ ሰዎች የጸበል ብዛትም ይሁን የሆድ እክል ሲያስቸግራቸው ሽንት ቤት ገብተው ጉዳያቸውን ፈጽመው እንደወጡ ሽንት ቤቱ ፈረሰ፡፡ ወይም በቀላል ቋንቋ ሰጠመ።
ነገር ግን አንድም ሰው ላይ አደጋ አለማጋጠሙ ትልቅ ድንቅ ተአምር ነበር ፡፡ እንዴት ብትሉ????
ከመጨረሻዎቹ ወንድ ተጠቃሚዎች መሀከል አንዱ ሽንት ቤቱ ከመሰጠሙ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት እዛ ሆኖ ዛሬ ይቺን ሽንት ቤት ምን ያርገበግባታል?? ሲል እንደነበር የሰሙት ሰዎች ነግረውኛል።
በተለይ ሽንት ቤቱ ሲፈርስ የተፈጠረው ድምጽ የጸሎት አዳራሽ በመሰማቱ ጸሎቱን ከደጅ ከሚሳተፉት መሃከል ሰው አብሮ ሰጥሞ ይሆናል ያሉ የተወሰኑ ሰዎች እየተራራጡ ሽንት ቤቱ ቢደርሱ እዛው የነበረችው የመጨረሻዋ ተጠቃሚ በኩራት ( በኮንፊደንስ ) አትደንግጡ እኔነኝ የመጨረሻዋ
ተጠቃሚ ብላ መጪውን ሰው አታረጋጋውም!!!!!!!! ድንቅ የእግዚአብሔር ተዓምር አትሉም???
ወይ አርሴማ በደጇ መጥቶ የሚማጸነውን ትፈውሳለች እንጂ ሽንት ቤት እንደማትጨምር አረጋግጣ ተአምሯን አሳየች!!!!!!!
ደብሯ ከጸበል አገልግሎት ውጪ በዋናነት የአርምሞ የሱባኤ ስፍራ ናት ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጁ ሁለት ዋሻዎች አሉ ፡፡
አንደኛው በጣም ሞቃት ሲሆን ሌላኛው በጣም ቀዝቃዛ ነው
በዋሻው የቆይታ ጊዜ በቀን መውሰድ የሚቻለው አንድ በውኃ የራሰ እፍኝ ሽንብራ እና አንድ ኩባያ በሶ ብቻ ይሆናል ውኃ የሚፈልግ በሶውን ትቶ በአንድ ኩባያ ውኃ መቀየር ይችላል።
በቅደስት አርሴማ የቆይታ ጊዜው ከሌሎች የሱባኤ
ስፍራዎች ይለያል። መልስ ያገኘ በማግስቱም ይወጣል ያላገኘ ወይም ቆይ የተባለ ደግሞ ይቆያል ነገር ግን የሱባኤው ትንሹ ቀን ሶስት ቀን ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል ፡፡
ሱባኤ መግባት አብዛኛው ሰው የሚያደርገው የተለመደ ጉዳይ ሲሆን ይልቁን መንፈሳዊ ልምምድ የሌላቸው ጫትና መጠጥ ትተው አሁን እንደመጡ አደራሽ ውስጥ ሲናገሩ የሰማኋቸው አፋቸው ላይ ጨርቃቸውን አስረው በዚህ ቅዱስ ስፍራ ሳያቸው
መለወጣቸው አስገርሞኝ ኦርትዶክስ ለዘላለም ትኑር ብዬ ልጮህ ከጅሎኝ ነበር ፡፡ ነገር ግን እኔም አርምሞ ላይ መሆኔ ትዝ ሲለኝ........ ተውኩት
በነገራችን ላይ የዋሻው የውስጠኛው ክፍልን አላስተዋወቅካችሁም አይደል ??? ዋሻው ከውስጡ ሲታይ የሚመስለው......... ይቅርታ......ተውት...... ለካ ዋሻው ይታያል እንጂ አይተረክም።

Не удается загрузить Youtube-плеер. Проверьте блокировку Youtube в вашей сети.
Повторяем попытку...
ድንቅ ነው የሚሰግዱ ድንጋዮች ያሉበት ጅሩ ቅድስት አርሴማ

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио

Похожие видео

ሰበር ዜና: የካቲት 18/2018 | Ethiopia News Today, Wed, Feb/25 February 2026

ሰበር ዜና: የካቲት 18/2018 | Ethiopia News Today, Wed, Feb/25 February 2026

የሰማዕቷ ዘንባባ ከሌባ ያዳናቸው ባልና ሚስት ! በፀበሏ አይናቸው የበራ እና ብዙ የተደረገላቸው | ጅሩ ቅድስት አርሴማ ገዳም

የሰማዕቷ ዘንባባ ከሌባ ያዳናቸው ባልና ሚስት ! በፀበሏ አይናቸው የበራ እና ብዙ የተደረገላቸው | ጅሩ ቅድስት አርሴማ ገዳም

EOTC TV  | ከተከዜ ሰማይ ሥር | ባለሥልጣናትን ያስደነገጠው ገዳም | ክፍል 1

EOTC TV | ከተከዜ ሰማይ ሥር | ባለሥልጣናትን ያስደነገጠው ገዳም | ክፍል 1

ሰበር//ዋና ከተማ በፋኖ ተያዘ!ዋና ዋና አዛዦች ተያዙ!ስልሳ ሽህ ተተኳሽና መሣሪያ በፋኖ እጅ ገባ!አሁናዊ አጫጭር የግንባር መረጃዎችና ዘገባዎች

ሰበር//ዋና ከተማ በፋኖ ተያዘ!ዋና ዋና አዛዦች ተያዙ!ስልሳ ሽህ ተተኳሽና መሣሪያ በፋኖ እጅ ገባ!አሁናዊ አጫጭር የግንባር መረጃዎችና ዘገባዎች

መኪና ውስጥ ሆኜ ደሜ እንደ ውሃ ይፈስ ነበር | ቅድስት አርሴማ ... !!! #comedianeshetu #ethiopia #arsema #አርሴማ

መኪና ውስጥ ሆኜ ደሜ እንደ ውሃ ይፈስ ነበር | ቅድስት አርሴማ ... !!! #comedianeshetu #ethiopia #arsema #አርሴማ

ንስሐ ሲገባ እንዴት ብሎ ነው የሚገባው ? ምን ምን ያስፈልጋል ? ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ/Aba Gebrekidan Girma New

ንስሐ ሲገባ እንዴት ብሎ ነው የሚገባው ? ምን ምን ያስፈልጋል ? ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ/Aba Gebrekidan Girma New

🛑ድንቅ ነው ጅሩ ቅድስት አርሴማ ተዓምር ተሰራ// ተዓምረኛው ዘንባባ#ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ

🛑ድንቅ ነው ጅሩ ቅድስት አርሴማ ተዓምር ተሰራ// ተዓምረኛው ዘንባባ#ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ

🔴 በሰሞኑ አነጋጋሪ ጉዳይ ላይ ቀሲስ ዘበነ መልስ ሰጡበት

🔴 በሰሞኑ አነጋጋሪ ጉዳይ ላይ ቀሲስ ዘበነ መልስ ሰጡበት

ታላቁን ጸሎት ሰይፈ ሥላሴን እንዴት እንጸልይ? በጸሎቱ ጥቅም ዙሪያ የተሰጠ ሰፊ ማብራሪያ!

ታላቁን ጸሎት ሰይፈ ሥላሴን እንዴት እንጸልይ? በጸሎቱ ጥቅም ዙሪያ የተሰጠ ሰፊ ማብራሪያ!

አቡነ ሐራ ድንግል  እና  ዋሻ ቅዱስ ሚካኤል  አያት ጣፎ እባብ ከሆዷ ወጣ ዛሬ የምናሳያችሁ ነብር እና ሚዳቋን የታረቁበት።

አቡነ ሐራ ድንግል እና ዋሻ ቅዱስ ሚካኤል አያት ጣፎ እባብ ከሆዷ ወጣ ዛሬ የምናሳያችሁ ነብር እና ሚዳቋን የታረቁበት።

"ስትመጣ እግሯ የለም".. ሲሪንቃ አርሴማ ....በተዓምራት የተሞላችሁ ሲሪንቃ አርሴማ ......ዘፍሬ ሕይወት ቅድስት አርሴማ የእናቶች ገዳም

ኢትዩጲያ በብልፅግና መዳፍ!  26 February 2026

ኢትዩጲያ በብልፅግና መዳፍ! 26 February 2026

የቅድስት አርሴማ አስደናቂ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) ​@Meba_tv

የቅድስት አርሴማ አስደናቂ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) ​@Meba_tv

🔴ጅሩ ቅድስት አርሴማ ገዳም #youtubeshorts #ኢትዮጵያ #ተዋሕዶ#ኦርቶዶክስ🔴ክፍል1

🔴ጅሩ ቅድስት አርሴማ ገዳም #youtubeshorts #ኢትዮጵያ #ተዋሕዶ#ኦርቶዶክስ🔴ክፍል1

አጋንንትን የሚያሳድድ ፀሎት ክፍል 1 ድንቅ እና ታላቅ ፀሎት የአጋንንት ዓይነቶች እና እነሱን ለመዋጋት የተወሰኑ ጸሎቶች

አጋንንትን የሚያሳድድ ፀሎት ክፍል 1 ድንቅ እና ታላቅ ፀሎት የአጋንንት ዓይነቶች እና እነሱን ለመዋጋት የተወሰኑ ጸሎቶች

ፀሎታችን እንዲሰማ እንዴት ብለን እንፀልይ? New Megabi Haddis Eshetu sebket

ፀሎታችን እንዲሰማ እንዴት ብለን እንፀልይ? New Megabi Haddis Eshetu sebket

ጅሩ ቅድስት አርሴማን ላስጎብኛችሁ  jieru kidest arsema

ጅሩ ቅድስት አርሴማን ላስጎብኛችሁ jieru kidest arsema

2ይ ዕለታዊ ዜና ስፖርት ረቡዕ 25 ለካቲት 2026፦ ካብ ሃገራዊት ጋንታ ኤርትራ ትጽቢትና ኣብ ቦትኡ ዝገብሮ ሮቛሒ // ቬኒሰስ ንማድሪድ የሕሊፉ ሳዕሲዑ

2ይ ዕለታዊ ዜና ስፖርት ረቡዕ 25 ለካቲት 2026፦ ካብ ሃገራዊት ጋንታ ኤርትራ ትጽቢትና ኣብ ቦትኡ ዝገብሮ ሮቛሒ // ቬኒሰስ ንማድሪድ የሕሊፉ ሳዕሲዑ

Студент 18 лет умер на 6 минут – Иисус показал, что ждёт Россию осенью 2026 года ⚠️

Студент 18 лет умер на 6 минут – Иисус показал, что ждёт Россию осенью 2026 года ⚠️

ከዛር መንፈስ ለመላቀቅ ይሄንን ወሳኝ ትምህርት ያድምጡ (

ከዛር መንፈስ ለመላቀቅ ይሄንን ወሳኝ ትምህርት ያድምጡ ("የዛር መንፈስን ለዘላለም መላቀቂያ ወሳኙ ሰባቱ መፍትሄዎች!")በመምህር ሄኖክ ተፈራ(ዘሚካኤል)።

© 2025 ycliper. Все права защищены.



  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности



Контакты для правообладателей: [email protected]