የአማራ ክልል የፍራፍሬ ልማት እመርታ
Автор: Amhara Agriculture Bureau
Загружено: 2026-02-23
Просмотров: 72
Описание:
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የቡናና የፍራፍሬ ልማት የእመርታ ንቅናቄ ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑ ተገለፀ።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በተመረጡ ወረዳዎችና ቀበሌዎች የቡናና ፍራፍሬ ልማትን በሰፋፊ ሞዴል ክላስተሮች በማልማት እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት የወረደውን አቅጣጫ ለማሳካት የክልል የማኔጅመንት ቡድን አባላት የመስክ ድጋፍ አድርገዋል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው የሚመሩት የክልል የማኔጅመንት ቡድን አባላት በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በመገኘት ያለውን የሰፋፊ ክላስተር የፍራፍሬ ልማት የቅድመ ዝግጅት ስራ በአካል ደግፈዋል። የአመራሩ፣ የባለሙያውና የአርሶ አደሩ ተነሳሽነት የሚበረታታ ነው ብለዋ። በመስክ ምልከታው በከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ ፣ በጥሩ የሙያ ስብጥር እና በወረደው አቅጣጫ መሰረት የተጀመረ ሲሆን ይህ ወሳኝ ኢኒሸቲቭ ለክልላችን የኢኮኖሚ እድገት ዋና መውጫ መንገድ ከመሆኑም ባሻገር በ25 አመቱ አሻጋሪ የዕድገትና ዘላቂ ልማት ዕቅድ ዋና የትኩረት ማዕከል በመሆኑ በዚህ አመት ጥሩ መሰረት በማስቀመጥ እያሰፉ ለመሔድ በተሟላ ቅድመ ዝግጅትና ቅንጅት ስራውን መምራት እንደሚገባ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው አሳስበዋል::
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ ድረ-ገጽ https://www.aboa.gov.et ቴሌግራም https://t.me/AmharaBOA ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?... ዩትዩብ / @amharaagriculturebureau6055 ቲክቶክ / amhara.agricultur
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: