🔴የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ መዝሙር🔴ዓይነ ከርም መጥቼ ሳየው ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ ORTHODOX MEZMUR (Lyrics) ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር
Автор: Orthodox Lyrics | ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር
Загружено: 2024-07-06
Просмотров: 24684
Описание:
እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ሰኔ 30 ልዱቱ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ +
ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
+የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
+ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
+የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
=መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
+የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
+በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
+በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
+እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
+የጌታችንን መንገድ የጠረገ
+ጌታውን ያጠመቀና
+ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
+ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::
ሰብስክራይብ በማደረግ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ሼር በማድረግ ድጋፎትን ያሳዩ።
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ይህ ገፅ የተከፈተው ኦርቶዶክሳዊ የመዝሙር ግጥሞችን በቀላሉ እንዲያገኙ ነው። ሰብስክራይብ በማድረግ እንዲሁም ሼር በማድረግ ይደግፉን።
In the name of God, the Son of God, the Holy Spirit, Amen!
This page was opened for you to easily find Orthodox hymns. Support us by subscribing and sharing.
🔴የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መዝሙር ያዳምጡ🔴
• 🔴የእመቤታችን መዝሙር🔴 ''ደጅሽ ላይ ቆሜ''|''Dejesh lay ...
#ዓይነከርምመጥቼሳየው #Orthododxmezmur #ኦርቶዶክሳዊመዝሙር #orthodoxlyrics
#Orthodox_Tewahido
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: