ትንቢተ ዘካርያስ Amharic Audio Bible - Tinbite Zekariyas Bible
Автор: ethio dawit tube
Загружено: 2020-11-18
Просмотров: 6140
Описание:
like and subscribe በማድረግ ቻናላችንን ይደግፉ ያሳድጉ።
#Subscribe በማድረግ ቤተሰብ እንዲሆኑ በትህትና እንጋብዝዎታለን። ethio dawit tube
አስተያየታችሁን ጻፉልኝ
#ትንቢተ_ዘካርያስ #Amharic_Audio #Bible
ethio dawit tube #SUBSCRIBE
/ @ethiodawittube
የትንቢተ ዘካርያስ ጥንቅር፣ ይዘትና የትንቢት ቃሉ ትኩረት ምን ይመስላል?
ትንቢተ ዘካርያስ ከዐሥራ ሁለቱ ታናናሽ ነቢያት መጻሕፍቶች በስፋቱ ወይም ብዙ ምዕራፎች በማከተቱ ትልቁና የመጀመሪያ ያደርገዋል፡፡ ጸሐፊው፣ የተጻፈበት ትክክለኛ ጊዜ፣ የመጽሐፉ ወጥነትና የመጽሐፉ ይዘት በተመለከተ ግን ከሁሉም የነቢያት መጻሕፍቶች በላይ የተወሳሰበ መሆኑን በመጽሐፉ ዙሪያ ጥናታቸው ያደርጉ ሊቃውንት ይገልጻሉ፡፡ ከመጽሐፉ ይዘት በደንብ መረዳት እንደሚቻለው ትንቢተ ዘካርያስ ግልጽ የሆኑ ሁለት ክፍሎች አሉት፡፡ እነዚህም ከምዕራፍ 1-8 እና ከ9-14 ናቸው፡፡ የመጽሐፉ የመጀመሪያው ክፍል ከባቢሎን ስደት በኋላ ኢየሩሳሌም በድጋሚ ትታደስበት ወይም ትገነባበት በነበረበት ወቅት በራሱ በዘካርያስ የተጻፈ ሲሆን ሁለተኛው ክፍል ግን ከብዙ ዓመታት በኋላ ሌሎች አጠናቅረው መጽሐፉ ውስጥ ያካተቱት እንደሆነ ከይዘቱና ከአጻጻፍ ስልቱ መረዳት ይቻላል፡፡ መጽሐፉ የተጻፈው የባቢሎናውያን አገዛዝ ወደ መውደቂያው አካባቢና በእነዘሩባቤል አማካይነት የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ የመታደስ ሥራ መጀመሪያው አካባቢ ነው፡፡ ይህም ማለት ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስት መቶ ሃያ እስከ አምስት መቶ ዐሥራ ስምንት አካባቢ እንደሆነ ከመጽሐፉ መረዳት ይቻላል(4፡6-10፤ 6፡12-13)፡፡
የመጽሐፉ የመጀመሪያው ክፍል (ዘካ 1-8) በራእይ የተሞላ ሆኖ ስለ ኢየሩሳሌም መታደስ፣ ስለ ቤተ መቅደሱ በድጋሚ መሠራት፣ ስለ እግዚአብሔር ሕዝብ መንጻት፣ እግዚአብሔር ስለሚቀበለው ትክክለኛ ጾምና ወደፊት ስለሚመጣው የመሲሑ ዘመን የሚናገር ነው፡፡ በዚህም መሠረት ይህ የመጀመሪያው ክፍል ስምንት ራእዮች ያሉት ሲሆን ከራእዮቹ ውጪ ከስደት በሚመለሱትና በሚኖሩት የወደፊት ሕይወት ጋር የተያያዙ የተወሰኑ ትምህርቶች ተካተዋል፡፡ እነዚህ ራእዮች አብዛኛው ትኩረታቸው በስደተኛው ሕዝብና በኢየሩሳሌም የወደፊቱ ብልጽግናና ክብር ላይ ያተኮሩ ሆነው አንዱ ከሌላው ተከታትለው የተገለጹ ናቸው፡፡
የመጽሐፉ ሁለተኛው ክፍል (ዘካ 9-14) አብዛኛውን ትኩረት ግን ስለሚመጣው መሲሕና ስለመጨረሻው ፍርድ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የዘካርያስ ስም ምንም አልተጠቀሰም፤ ተግባራቱ የተከናወኑበት ጊዜም ከመጀመርያው ክፍል ፈጽሞ የተለየ ወቅት ነው፤ ምንም ዓይነት የተጠቀሱ ቀናትም ይሁን የመሪዎች ስም የለም፤ ቤተ መቅደስም ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ላይ ሆኖ በተጠናከረ መልኩ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል(ዘካ 9፡8 ፤ 11፡13-14)፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ነቢዩ ራሱን እንደ ተመታና እንደ ተነቀፈ እረኛ ሆኖ ያቀርባል፤ ጸሐፊው የተጠቀማቸው ቃላትና ገለጻዎች ከመጀመርያው ክፍል የተለዩ ናቸው፡፡
ምንም እንኳ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ክፍል መካከል በቃላት አጠቃቀም፣ በአነጋገር ዘይቤአቸው፣ ባካተቷቸው ዋና ዋና የትንቢት ቃላት፣ ትንቢቱ በተነገሩበት የጊዜ ሁኔታ፣ በተካተቱት ገጸ ባሕርያቶች፣ በሚጠቅሷቸው ቦታዎች፣ በሚሰጡት ታሪካዊ መረጃዎችና በሌሎችም ተጨማሪ በሆኑ ነገሮች ላይ ግልጽ የሆነ ልዩነት ቢኖርም የሚገናኙበት የጋራ የሆኑ ብዙ ፍሬ አሳቦች እንዳሉም ግልጽ ነው፡፡
ግሩም የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል የሆነውን ሙሉ ትረካውን ሰምተው ሲጨርሱ like. እንዲሁም ለወዳጅ ዘመድ share እና አስረያየቶን በመስጠት ይደግፉን።
#ትንቢተ_ዘካርያስ
• ትንቢተ ዘካርያስ Amharic Audio Bible - Tinbite Z...
#ሰቆቃው_ኤርምያስ
• ሰቆቃው ኤርምያስ Amharic Audio Bible - Sekokaw E...
#ትንቢተ_ኢዩኤል
• ትንቢተ ኢዩኤል Amharic Audio Bible - Tinbite Ey...
#ትንቢተ_አብድዩ
• ትንቢተ አብድዩ Amharic Audio Bible - Tinbite Ab...
#ትንቢተ_ናሆም
• ትንቢተ ናሆም Amharic Audio Bible - Tinbite Nah...
#ትንቢተ_ሚክያስ
• ትንቢተ ሚክያስ Amharic Audio Bible - Tinbite Mi...
#ትንቢተ_ሶፎንያስ
• ትንቢተ ሶፎንያስ Amharic Audio Bible - Tinbite S...
#ትንቢተ_ሚልኪያስ
• ትንቢተ ሚልኪያስ Amharic Audio Bible - Tinbite M...
#መጽሃፈ ነገስት ቀዳማዊ
• መጽሃፈ ነገስት ቀዳማዊ Amharic Audio Bible - Mesi...
#መጽሐፈ_መክብብ
• መጽሐፈ መክብብ Amharic Audio Bible - Metsihafe...
#መጽሃፈ_እያሱ ወልደ ነዌ
• መጽሃፈ እያሱ ወልደ ነዌ Amharic Audio Bible - mesi...
#መጽሃፈ_ሳሙኤል ቀዳማዊ
• መጽሃፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ Amharic Audio Bible - Mesih...
#መጽሃፈ_ሳሙኤል ካልዕ
• መጽሃፈ ሳሙኤል ካልዕ Amharic Audio Bible - Mesiha...
#ትንቢተ_ዳንኤል Amharic Audio Bible
• ሁሌም ቢሰማ የማይጠገብ ታሪክ ትንቢተ ዳንኤል Amharic Audio...
#መዝሙረ_ዳዊት ምዕራፍ 1-50
• Видео
#መጽሃፈ_ኢዮብ
• ♥መጽሃፈ ኢዮብ Amharic Audio Bible - Metsihaf...
#መጽሐፈ_ምሳሌ
• ♥መጽሐፈ ምሳሌ Amharic Audio Bible - Metsihafe...
#Tewodros_Yosef #Maryam_Fidel_Nat_Nu_Temaru #Tewahido
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: