የጥንተ ስቅለት ምሥጢር፡ ጥቅምት 27 የመድኃኔዓለም ታሪክና ትርጉሙ| ኢየሱስ ክርስቶስ| Medihanealem
Автор: በትረ-ጊዮርጊስ Betre Tube
Загружено: 2025-11-05
Просмотров: 357
Описание:
#መድኃኔዓለም #ጥንተስቅለት #ኢየሱስክርስቶስ #መስቀል #Medihanealem
በጥቅምት 27 የምናከብረው የመድኃኔዓለም በዓል፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥንተ ስቅለት ታሪክ በጥልቀት ይተርካል። በዚህ ቪዲዮ ውስጥ የሰው ልጅ ከኃጢአት ቀንበር ነፃ የወጣበትን ታላቅ የፍቅርና የመስዋዕትነት ታሪክ በዝርዝር እንመለከታለን። ይህ ትረካ በጌቴሴማኒ የጀመረውን የመከራ ጉዞ፣ በሐሰተኛ ፍርድ ፊት የደረሰበትን ክስ፣ በጲላጦስ አደባባይ የሕዝብ ዕውር ውሳኔ፣ የጎልጎታን መንገድ፣ በመስቀል ላይ የፈሰሰውን ደም፣ እና የፍጥረትን ምላሽ በዝርዝር ያቀርባል። የመስቀሉ ዘላለማዊ መልእክት፡ የፍቅር ማዕረግ፣ የድል ክብር! ይህን ታላቅ የፍቅር እና የድል መልዕክት ከዓለም ጋር ለመካፈል፣ ላይክ፣ ሼር እና ሰብስክራይብ ያድርጉ!
As the March 27 Crucifixion is celebrated during the Great Lent, we delve deep into God's immense love, the sacrifice of our Lord Jesus Christ, and the story of humanity's liberation from the bondage of sin. This narration meticulously covers the journey of suffering that began in Gethsemane, the false accusations before the fake judgment, the blind decision of the crowd in Pilate's courtyard, the Road to Golgotha, the blood shed on the cross, the silence of the Father, and creation's response. The eternal message of the Cross: the glory of love, the honor of victory! To share this great message of love and victory with the world, like, share, and subscribe!
በታሪኩ ውስጥ የሚገኙ ጥቅሶችን ከዚህ ቀጥሎ ማግኘት ይቻላል።
ማቴዎስ 26፡38: "ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ ከእኔ ጋርም ንቁ"
ሉቃስ 22፡42: "አባት ሆይ፥ ብትወድስ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን እንደ አንተ ፈቃድ እንጅ እንደ እኔ አይሁን"
ማቴዎስ 26፡40: "አንድ ሰዓት እንኳ ከእኔ ጋር ትጠብቁ ዘንድ አልቻላችሁምን? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ናት"
ማቴዎስ 26፡53: "አሥራ ሁለት ጭፍራ መላእክት አሁኑኑ አባቴ እንዲሰጠኝ መጠየቅ እንደምችል አታስብምን?"
ማቴዎስ 26፡52: "ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ፤ ሰይፍ የሚያነሱ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና"
ዮሐንስ 3፡16: "በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይዎት እንዲኖረው እንጅ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪስጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና"
ዮሐንስ 2፡19: "ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን እሠራዋለሁ"
ማቴዎስ 26፡63: "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ንገረን"
ማቴዎስ 26፡62: "መቼም አትናገርም? እነዚህስ በአንተ ላይ የሚመሰክሩት ምንድር ነው?"
ማርቆስ 14፡62: "እኔ ነኝ፤ ከእንግዲህም የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ተቀምጦ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ"
ማቴዎስ 26፡65: "ሌላ ምስክሮች ምን ያስፈልጉናል? እነሆ፥ የስድቡን ቃል ሰምታችኋል"
ሉቃስ 22፡64: "ክርስቶስ ሆይ፥ የመታህ ማን እንደሆነ ንገረን"
ሉቃስ 22፡61-62: (ጴጥሮስ የካደበት እና ያለቀሰበት ክፍል)
ዮሐንስ 18፡33: "አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?"
ዮሐንስ 18፡36: "መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴስ ከዚህ ዓለም ብትሆን ኖሮ፥ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም"
ዮሐንስ 18፡38: "በእርሱ ዘንድ ምንም በደል አላገኘሁም"
ሉቃስ 23፡18: "ይህንን አንፈልግም፥ በርባንን እንጂ!"
ዮሐንስ 19፡3: "የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላምታ ይገባሃል!"
ዮሐንስ 19፡5: "እነሆ ሰውዬው!"
ሉቃስ 23፡21: "ስቀለው! ስቀለው!"
ማቴዎስ 27፡19: "ያን ጻድቅ ሰው ምንም አታድርገው"
ማቴዎስ 27፡24: "እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተመልከቱት"
ሉቃስ 23፡28: "የእየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ እንጂ ለእኔ አታልቅሱ፤"
1 ጴጥሮስ 2፡22: "ምንም ኃጢአት ያላደረገው፣ በከንፈሩም ተንኮል ያልተገኘበት"
ኢሳይያስ 53፡12: "ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጠረ"
ሉቃስ 23፡34: "አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው"
ማቴዎስ 27፡42: "ሌሎችን አድኖአል፤ ራሱን ማዳን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ፥ እኛም እናምንበታለን"
ሉቃስ 23፡39-41: "አንተ ክርስቶስ አይደለህምን? ራስህንም እኛንም አድን" / "አንተ እንኳ በተመሳሳይ ፍርድ ሳለህ እግዚአብሔርን አትፈራምን? እኛስ ቅጣታችን የተገባ ነው፤ እርሱ ግን ምንም ክፉ አላደረገም"
ሉቃስ 23፡43: "እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ"
ዮሐንስ 19፡26: "አንቺ ሴት ሆይ፥ እነሆ ልጅሽ! ለእርሱም እነኋት እናትህ"
ማቴዎስ 27፡46: "ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ሲል፥ ትርጓሜውም አምላኬ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? ማለት ነው።"
ዮሐንስ 19፡28: "ተጠማሁ"
መዝሙር 69፡21: "ለምግቤ ከርቤ ሰጡኝ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ"
ሉቃስ 23፡46: "አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ"
ዮሐንስ 19፡30: "ተፈጸመ!"
ማቴዎስ 27፡51-53: (ምድር የተንቀጠቀጠችበት፣ መቃብሮች የተከፈቱበት ክፍል)
ማቴዎስ 27፡54: "ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበር"
2 ቆሮንቶስ 5፡21: "ኃጢአትን የማያውቀውን እርሱን እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው"
1 ቆሮንቶስ 6፡20: "በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ሥለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።"
ሮሜ 5፡8: "እኛ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስመሰክራል"
ዮሐንስ 15፡13: "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር ከማንም የለም"
1 ቆሮንቶስ 6፡20: "በዋጋ ተገዝታችኋልና፤ ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ"
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: