ሙሉ ፡ መስዋዕት - Azeb Hailu - Cover by
Автор: Amen Studio
Загружено: 2025-12-29
Просмотров: 551
Описание:
ሙሉ ፡ መስዋዕት ፡ እንከን ፡ የሌለው ፡ ኦሆ
ለአማልክት ፡ አምላክ ፡ ይዣለሁ ፡ ይኸው ፡ አሃ
የማያነክስ ፡ ወይ ፡ ያልታወረ ፡ ኦሆ
ለጌቶች ፡ ጌታ ፡ ለተከበረ ፡ አሃ
በፊቱ ፡ የተወደደ ፡
በፊቱ ፡ ከቶ ፡ ያልተናቀ
ሊያሸተው ፡ በአምላኬ ፡ ዘንድ ፡
ዘወትር ፡ የተናፈቀ
ቅዱሱም ፡ ሕያው ፡ መስዋዕት ፡
እራሴ ፡ ነው ፡ ሰውነቴ
ላፍስሰውና ፡ ልሰዋው ፡
ደስ ፡ ይበለው ፡ መድኃኒቴ
አዝ፦ ለአምላኬ ፡
ምሥጋናዬን ፡ እሰዋለሁ
ለንጉሡ ፡
ስዕለቴን ፡ እከፍላለሁ
ይህ ፡ ለእኔ ፡
ሥራዬ ፡ ነው ፡ ልማዴ
በወቅቱ ፡
ክብርን ፡ መስጠት ፡ ለውዴ
ይሄ ፡ ነው ፡ ልማዴ (፫x)
ሙሉ ፡ ለሙሉ ፡ ጭሶ ፡ የሚቃጠል ፡ ኦሆ
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ እሰይ ፡ የሚያስብል ፡ አሃ
ያለቁጠባ ፡ ያለ ፡ ስስት ፡ ኦሆ
በማደሪያው ፡ ላይ ፡ ይሽተትለት ፡ አሃ
ከነፍሴ ፡ ከፍፁም ፡ ደስታ ፡
የነፍሴ ፡ ነው ፡ ከፍቃዴ
በጠዋትና ፡ በማታ ፡
የምሰዋለት ፡ ለውዴ
የተመረጠውን ፡ መስዋዕት ፡
ከስቡ እና ፡ ከበኩሩ
አምላኬን ፡ ደስ ፡ ካሰኘው ፡
ይኸው ፡ ለዝናው ፡ ለክብሩ
አዝ፦ ለጌታ ፡
ምሥጋናዬን ፡ እሰዋለሁ
ለልዑሉ ፡
ስዕለቴን ፡ እከፍላለሁ
ይህ ፡ ለእኔ ፡
ሥራዬ ፡ ነው ፡ ልማዴ
በወቅቱ ፡
ክብርን ፡ መስጠት ፡ ለውዴ
ይሄ ፡ ነው ፡ ልማዴ (፫x)
የደመናትን ፡ ድንበር ፡ የሚጥስ ፡ ኦሆ
ወደ ፡ ማደሪያው ፡ የሚገሰግስ ፡ አሃ
የተወደደው ፡ ውድ ፡ ምሥጋና ፡ ኦሆ
የተገባው ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ አሃ
በምድር ፡ እስካለሁባት ፡ እስከ ፡ ኖርኩባት ፡ ዘመኔ
የሚገባውን ፡ በሙሉ ፡ አላጓድልም ፡ ከእኔ
በማንኛውም ፡ ሁኔታ ፡ በማንኛውም ፡ ሰዓት
እርሱ ፡ ይቀበለኝ ፡ እንጂ ፡ አልሰለችም ፡ መሰዋት
አዝ፦ ለአምላኬ ፡
ምሥጋናዬን ፡ እሰዋለሁ
ለንጉሡ ፡
ስዕለቴን ፡ እከፍላለሁ
ይህ ፡ ለእኔ ፡
ሥራዬ ፡ ነው ፡ ልማዴ
በወቅቱ ፡
ክብርን ፡ መስጠት ፡ ለውዴ
ይሄ ፡ ነው ፡ ልማዴ (፭x)
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: