Cove songe አፄ ቴድሮስ ቴዲ
Автор: Fert tube
Загружено: 2026-01-26
Просмотров: 673
Описание:
...........................
የሰገደላት ውበቱ ፤ ያቺን የቃል መስታይት
ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ ፤ ቆሞ ስቃዩዋን ላለማየት
የወደቀላት ውበቱ ፤ ያቺን የቃል መስታይት
ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ ፤ ቆሞ ስቃዩዋን ላለማየት
ደርሶ ባያስጥለው ፤ ገብርዬ ከስለት
ጀግናው ተፈተነ ፤ በመቅደላ አቀበት
ተዋከበና ፤ ተዋከበና
ወዲህ ዞር ፤ ቢል ሰው የለምና
ገብርዬ ሲወድቅ ፤ ቀኙ ዛለና
አረሩን ስቦ ፤ ጠጣው ያ ጀግና
ደርሶ ባያስጥለው ፤ ገብርዬ ከስለት
ጀግናው ተፈተነ ፤ በመቅደላ አቀበት
ተዋከበና ፤ ተዋከበና
ወዲህ ዞር ቢል ፤ሰው የለምና
የነደደ እሳት ፤ ክንዱን ተ'ርሶ
ጨክኖ ካሣ ፤ ጋተና ኮሶ
ሞተ 'ላንድ አገር ፤ ባንዲራ ለብሶ
......................
ካሳ በል አንሳ እንደ አንበሳ
የቋራ አንበሳ ዳግማሮስ ካሳ በል አንሳ
ካሳ በል አንሳ እንደ አንበሳ
የአንድነት አገር ክብሯ ከቶም ሳይረሳ
ካሳ በል አንሳ እንደ አንበሳ
ንቃ በመንፈስ ላንድነት ካሣ ተነሳ
ካሳ በል አንሳ እንደ አንበሳ
አንተ የሞትክላት አገር ክብሯ ሳይረሳ
ካሳ በል አንሳ እንደ አንበሳ
..............................
ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር
ያንዲት ኢትዮጵያ ፤ ዋልታና ማገር
ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
አገር ሊያቆም ነው ቴዎድሮስ ወድቆ
እረረረረረ
አምጡ ቆርጣችሁ ፤ ከሹሩባው ላይ
ኪዳን እንሰር፤ እንዳንለያይ
ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
አገር ሊያቆም ነው ፤ ቴዎድሮስ ወድቆ
አረጀች እያሉ ሰዎቹ ሲያሙሽ(2x)
ሙሽራ ነሽ ጎንደር ይሰፋል ልብስሽ
ፊት ለፊት ፊት ለፊት
ሳይገላገለው ህልሙን በሆድ ይዞ
ሳይገላገለው ሽሉን በሆድ ይዞ
የሚረዳው አጥቶ ነው ብቻውን ተክዞ
ተክዞ ተክዞ
ስንቱን በሆድ ይዞ
የወገቡን እሳት ካፎቱ ላይ መዝዞ(2x)
ጠጥቶላት ሞተ ክንዱን ተንተርሶ
አያሳዝንም ወይ
እርርርርርርርርርርር
ካሣ ካሣ የቋራው አንበሣ(2x)
ዳኘን ዳኘን አንድ ህልም አሳየን(2x)
............................
ዝግባ ሚያሳክለን አንድ ፍቅር አጥተን
ዝግባ ሚያሳክለን አንድነትን አጥተን
ከፊት የነበርነው ከሰው ኋላ ቀርተን
አናሳዝንም ወይ
እርርርርርርርርር
ጎንደርና ጎጃም ፤ ወሎና ትግራይ(2x)
ኦሮሞና ተጉለት ሆነን አንድ ላይ
ጉራጌና ሃረር ዶርዜ ወላይታ
ቤኒሻንጉል ሶማሌ አፋር አሳይታ
ግመሌን ላጠጣት እንደ አፋር ተጉዤ
ግመሌን ላጠጣት ቀይ ባህር ተጉዤ
አንድ ገመድ አጣሁ ልመልሳት ይዤ
እረረረረ እረረ
'ያንዲት እናት ልጆች መሆናችን አውቀን
ጎሳና ኃይማኖት ሳይነጣጥለን
ምን ይሳነን ነበር ብንተባበር
አናሳዝንም ወይ
እርርርርርርር
ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር
ያንዲት ኢትዮጵያ ፤ ዋልታና ማገር
ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
አገር ሊያቆም ነው ፤ ቴዎድሮስ ወድቆ(3x)
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: