ያልተነገረው የበላይ ዘለቀ ጀግንነት ኢትዮጵ ...ትናንት... ዛሬ... ነገ ..የታሪክ ማስታወሻችንን ያድምጡት
Автор: Maleda tvnetwork
Загружено: 2021-01-25
Просмотров: 17014
Описание:
#Maledatvnetwork #ethiopian #history#BelayZeleke ያልተነገረው የበላይ ዘለቀ ጀግንነት ኢትዮጵ ...ትናንት... ዛሬ... ነገ ..የታሪክ ማስታወሻችንን ያድምጡት
ከበላይ ጋር በጀግንነት አብሮ የተዋደቀው የጎጃም ሰው ለበላይ ከገጠመለት አያሌ ሙገሳዎች ከፊሎቹ የሚከተሉት ናቸው...
ጎጃም ባርበኝነት እንደምን ታወቀ፣
ያ በታች ዝቅ ሲል ያ በላይ ዘለቀ፤
***
ያ በላይ ዘለቀ የለምጨን በርበሬ፣
ጠላት ተሸበረ እየሰማ ወሬ፤
***
ጎጃም ዓይኑን ታሞ ሲደነባበር፣
የለምጨኑ አንበሳ ይመራው ጀመር፤
***
የለምጨኑ አንበሳ፣
መጣሉ እያገሳ፤
የሸበል ንጉሥ፣
ገባሉ ማርቆስ።
***
አባ ኮስትር በላይ የለምጨኑ አንበሳ እባክህ ተቆጣ፣
አንተም ራስ ተባል እኛም ጎጆ እንውጣ፤
***
ፈረንጅ ምድር ለቆ ቢሄድ በሰማይ፣
የጎጃሙ አንበሳ ዳመናውን አልፎ ዘለቀ በላይ።
***
ጣሊያን ፍየል ሆኖ ቅጠል ቅጠል ሲያይ፣
የለምጨኑ አንበሳ ነብር ተመስሎ አረደው በላይ።
***
የጎጃሙ ነብር የለምጨኑ አንበሳ፣
አባ ኮስትር በሌ እንደምን ይረሳ።
***
ሰላሳ ደጃዝማች አምሳ ፊታውራሪ ያስቀመጠውን፥
ጭልጥ አርጎ ጠጣው በላይ ብቻውን።
***
ያ በላይ ዘለቀ የጦር አጋሠሥ፣
ባንድ ቀን ያስገባል መቶ መትረየስ።
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: