ESSEY YOHANNES /ምስክር/ "MESEKER" New Ethiopian Gospel Song /2024
Автор: Essey Yohannes Official
Загружено: 2024-12-06
Просмотров: 13302
Описание:
“ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሣማ!”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥13
በኩራት ላንቀላፉት ትንሣኤ፣
ህይወት እንዲቀጥል ሆነሃል መንስኤ፣
ብንሞት እንደማንቀር በምድር፣
ተነሥተህ ያሳየሀን ምስክር።
፩, የሚጠፋው የማይጠፋውን፣
የሚሞተው የማይሞተውን፣
ሊነሣ ለብሶ፣
ዳግም ታድሶ፣
ከሞት በኋላ፣
ከዚህኛው ሌላ፣
ህይወት ለመኖሩ፣
አንተው ምስክሩ።
ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ፣
ባንተ በኩል ትንሣኤ ተሰጠ ፣
ከሙታን የተነሣህ ፊተኛ፣
ኢየሱስ ተስፋችን ነህ ለኛ።
፪,ልዑል ነህ ለኛ መጠጊያ፣
የረታህ የሞትን መውጊያ ፣
ሙታን እንዲነሡ ማረጋገጫ፣
በእምነት የምታስሮጠን የያዝነዉን ሩጫ።
ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ፣
ባንተ በኩል ትንሣኤ ተሰጠ ፣
ከሙታን የተነሣህ ፊተኛ፣
ኢየሱስ ተስፋችን ነህ ለኛ።
፫,የኋለኛው መለከት ሲነፋ፣
ሁላችን አናንቀላፋ ፣
እንለወጣለን በቅጽበተ ዓይን፣
በርግጥ ተስፋ አለን ልናይ ሰማይን።
ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ፣
ባንተ በኩል ትንሣኤ ተሰጠ ፣
ከሙታን የተነሣህ ፊተኛ፣
ኢየሱስ ተስፋችን ነህ ለኛ።
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: