በአንተ ፊት || MARANATHA CHOIR || Apostolic Song || Amen || Apostolic church of Ethiopia
Автор: ሰማያዊ ሚዲያ- Semayawi Media
Загружено: 2025-10-30
Просмотров: 447
Описание:
በአንተ ፊት
ትችላለህ መለወጥ
ትችላለህ ማስዋብ
ትችላለህ መቀየር
ትችላለህ ነገርን
በአንተ ፊት የቆየ እንዲሁ አይመለስ ፊትህ የተንበረከከ
በአንተ ፊት ያነባ እንዲሁ አይመለስ ፊትህን የፈለገ
አመድን ነስንሶ እራሱን አዋርዶ
በተሰበረ ልብ አንባውን አፍስሶ
የፈለገህ በእጥፍ ይቀበላል
እራሱን አትርፎ ለሌላም ይተርፋል
ምንም እንኳን ቢሆን ያለ ህግ
በንጉስ ቀለበት ቢታወጅም አዋጅ
በፀሎት የቆየ በአንተ ፊት በእንባ
ታሪክ ተቀይሮ ይደርባል ካባ
ሕዝቡን ይታደጋል ኦሆ ኦሆ ወገኑን ያድናል
ታሪክ አስግልብጦ ኦሆ ኦሆ ከሞት ይመልሳል
ፀጋን ተቀብሎ ኦሆ ኦሆ ለሌላ ይተርፋል
ቃልኪዳን ስላለው እህ እህ ምድርን ይወርሳል
ክብሬ ነህ ላለህ ክብር ነሀ
ሞገሴ ላለህ ሞገስ ነህ
ለታመኑብህ ጋሻ ነህ
አያፍርም አንተን የያዘ ሰው
አይወድቅም የተደገፈህ
አያፍርም አንተን የታመነ
አይወድቅም ፊትህን የፈለገ (እጅህን የለመደ)
#amen #duet #habesha #music #love #ebs #motivation #song #africa #apostolicchurch
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: