ycliper

Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
Скачать

ኢየሱስ አባቴ ብሎ መጥራቱ ልክ ነው ወይስ አይደለም? ኢትዮጵያዊው በኬንያ ዶክተር ዛኪር ናይክን አስጨነቀው

Автор: እውነት ያሳርፋል Ewnet Yasarfal

Загружено: 2025-01-30

Просмотров: 75274

Описание: የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇
   / @dhugaanniboqachiisa  

መልካም ዜና

የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን።

ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡-
“በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።”

መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡-

“ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥...
እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15)

ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል።

ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”
— (ኢሳይያስ 53፥10)

ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና።

{የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29)

እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው።

1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል።

2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ።

አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇
http://t.me/BibleAndMe
Additional: - [email protected]

Не удается загрузить Youtube-плеер. Проверьте блокировку Youtube в вашей сети.
Повторяем попытку...
ኢየሱስ አባቴ ብሎ መጥራቱ ልክ ነው ወይስ አይደለም? ኢትዮጵያዊው በኬንያ ዶክተር ዛኪር ናይክን አስጨነቀው

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио

Похожие видео

‘መሀመድ የ6 ዓመት ልጅ ማግባቱ ለህሊናዬ እስካሁን እረፍት አይሰጠኝም' ||Mohammed abebaw(መሐመድ አበባው) || #Meskelmedia#2025

‘መሀመድ የ6 ዓመት ልጅ ማግባቱ ለህሊናዬ እስካሁን እረፍት አይሰጠኝም' ||Mohammed abebaw(መሐመድ አበባው) || #Meskelmedia#2025

መሐመድን የገደለው ማን ነው? 10 ምክንያቶች || Who Killed Muhammad? [David Wood Amharic]

መሐመድን የገደለው ማን ነው? 10 ምክንያቶች || Who Killed Muhammad? [David Wood Amharic]

"ሁለት ቤቴን ለአላማዬ ስል ሽጫለው አሁን ቤት አልባ ነኝ ጤናዬም ታውኳል" /ሳቄን መልሱልኝ የሳቅ ንጉሱ በላቸው ግርማ/

በመሐመድ ሂጃብ እና በዴቪድ ዉድ መካከል የተደረገው ክርክር በቅንጭብታ || Mohammed Hijab's CAREER ENDING DEBATE Vs. David Wood

በመሐመድ ሂጃብ እና በዴቪድ ዉድ መካከል የተደረገው ክርክር በቅንጭብታ || Mohammed Hijab's CAREER ENDING DEBATE Vs. David Wood

እውነታን መካድ የማይችለው ሙስሊም የኢየሱስን አምላክነት በአደባባይ አመነ || Sam Shamoun Amharic

እውነታን መካድ የማይችለው ሙስሊም የኢየሱስን አምላክነት በአደባባይ አመነ || Sam Shamoun Amharic

የኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት በ53 ማስረጃዎች (ክፍል 1)

የኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት በ53 ማስረጃዎች (ክፍል 1)

የቁርአኗ ማርያም ማን ናት? ለምንስ የሷ ስም ብቻ ጎልቶ ተጻፈ? David Wood Amharic

የቁርአኗ ማርያም ማን ናት? ለምንስ የሷ ስም ብቻ ጎልቶ ተጻፈ? David Wood Amharic

ውይይቱ ባልታሰበ መንገድ ተቀየረ | faith in Jesus

ውይይቱ ባልታሰበ መንገድ ተቀየረ | faith in Jesus

Иран не примет перемирие? Скотт Риттер: война только начинается

Иран не примет перемирие? Скотт Риттер: война только начинается

ቸርች አቃ**ጥዬ አውቃለሁ♦️[ክፍል 1️⃣] |ኢየሱስ ባያገኘኝ ኖሮ…ሼህ አብዶ |ከእስ**ልምና ወደ ኢየሱስ |PistisPodcast @ABRAHAM_M7_MEDIA

ቸርች አቃ**ጥዬ አውቃለሁ♦️[ክፍል 1️⃣] |ኢየሱስ ባያገኘኝ ኖሮ…ሼህ አብዶ |ከእስ**ልምና ወደ ኢየሱስ |PistisPodcast @ABRAHAM_M7_MEDIA

1 ПРИВЫЧКА ПЕРЕД СНОМ — И ЖИВОТ ИСЧЕЗАЕТ! Висцеральный жир сгорает после 55

1 ПРИВЫЧКА ПЕРЕД СНОМ — И ЖИВОТ ИСЧЕЗАЕТ! Висцеральный жир сгорает после 55

የእስልምና ታሪካዊ አመጣጥ || መሐመድ ፣ መካ ፣ ቁርአን || Dr. Jay Smith Amharic

የእስልምና ታሪካዊ አመጣጥ || መሐመድ ፣ መካ ፣ ቁርአን || Dr. Jay Smith Amharic

ሌላ አስፈላጊ ጥያቄ በኬኒያ መድረክ ላይ ተጠይቋል ፣ መልሱም ያልተጠበቀ ነው ኬኒያ 2025 አዲስ Another unexpected question from Kenya

ሌላ አስፈላጊ ጥያቄ በኬኒያ መድረክ ላይ ተጠይቋል ፣ መልሱም ያልተጠበቀ ነው ኬኒያ 2025 አዲስ Another unexpected question from Kenya

ተውሂድ ወይስ ሥላሴ || እስልምና ወይስ ክርስትና || ትክክለኛው የቱ ነው? Dr. Shabir Ally and Dr. Nabeel Qureshi Debate ክፍል 1

ተውሂድ ወይስ ሥላሴ || እስልምና ወይስ ክርስትና || ትክክለኛው የቱ ነው? Dr. Shabir Ally and Dr. Nabeel Qureshi Debate ክፍል 1

ኢምራን አኬን ለማዋረድ ቢመጣም ራሱ ተዋርዶ ወጣ | በእስልምና ዙሪያ | ሐዋርያዊ መልሶች, Apostolic Answers, ዮሐድ ንጉስ

ኢምራን አኬን ለማዋረድ ቢመጣም ራሱ ተዋርዶ ወጣ | በእስልምና ዙሪያ | ሐዋርያዊ መልሶች, Apostolic Answers, ዮሐድ ንጉስ

ለ4ቱ ጥያቄዎቼ አጥጋቢ መልስ ከሰጠኸኝ እስልምናን እቀበላለሁ ፤ የክርስቲያኗ እህት 4 ወሳኝ ጥያቄዎች /The woman who have 4 questions

ለ4ቱ ጥያቄዎቼ አጥጋቢ መልስ ከሰጠኸኝ እስልምናን እቀበላለሁ ፤ የክርስቲያኗ እህት 4 ወሳኝ ጥያቄዎች /The woman who have 4 questions

Индонезийский проповедник бросил вызов доктору Закиру Найку!🔥

Индонезийский проповедник бросил вызов доктору Закиру Найку!🔥

Парень бросает вызов и утверждает, что он бог - Доктор Закир Найк

Парень бросает вызов и утверждает, что он бог - Доктор Закир Найк

Скотт Риттер: США и Израиль проигрывают войну с Ираном?

Скотт Риттер: США и Израиль проигрывают войну с Ираном?

ኢየሱስ ቃል በቃል አምላክ ነኝ አምልኩኝ ያለበት... || Sam Shamoun Amharic

ኢየሱስ ቃል በቃል አምላክ ነኝ አምልኩኝ ያለበት... || Sam Shamoun Amharic

© 2025 ycliper. Все права защищены.

  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности

Контакты для правообладателей: [email protected]