ከውርጃ በኋላ የወር አበባ መቼ መምጣት አለበት ? የደም መፍሰሱስ መቆም ያለበት መቼ ነው ? | period after abortion and bleeding
Автор: Dr. Amanuel - ዶ/ር አማኑኤል
Загружено: 2022-12-01
Просмотров: 51470
Описание:
📌ከሁለቱም አይነት ውርጃ በኋላ ከ1 እስከ 2 ሳምንታት የሚቆይ የደም መፍሰስ የተለመደ ነው። ለ አንዳንድ ሴቶች የደም ፍሰቱ ይቆምላቸዋል ከዚያም እንደገና ይጀምራል። ቢሆንም ከ 1 ወይም 2 ሳምንታት በኋላ የደም መፍሰሱ መቀነስ አለበት። ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ወይም እስከሚቀጥለው የወር አበባችሁ መቃረቢያ ድረስ ትንሽ የደም መፍሰስ ወይም ነጠብጣብ ሊፈሳችሁ ይችላል።
ከውርጃው በኋላ የሚፈሳችሁ ደም ከወር አበባችሁ ጋር ተመሳሳይ ነው። ቀለሙ የበለጠ ቡናማ ካልሆነ በስተቀር። ከህክምና ውርጃ ይልቅ የመድሃኒቱ ውርጃ የሚኖረው የደም ፍሰት በጣም ከባድ ነው። አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ደግሞ የደም መፍሰሱን የበለጠ ሊጨምሩ ወይም ሊቀንሱ ይችላሉ። ለምሳሌ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በምታደርጉበት ጊዜ ብዙ ደም ሊፈሳችሁ ይችላል። እረፍት ስታደርጉ ደግሞ ያነሰ ይሆናል።
ሌላው የረጋ ደምም ሊፈሳችሁ ይችላል። እናም ይህ የተለመደ ነው የሚያስጨንቅ ነገር አይደለም። clot ኦቹ ከትንሽ እስከ ትልቅ ሊሆኑ ይችላል።
ነገር ግን የደም መርጋቱ ከከፍተኛ የደም መፍሰስ ጋር ያለ ማቋረጥ ለሁለት ሰዓት የሚፈሳቹ ከሆነ ይሄን ጊዜ ጤና ጣቢያ መሄድ ይኖርባችኋል።
ሌላው ደግሞ ደም የቀላቀለ ፈሳሽም ሊፈሳችሁ ይችላል። ፈሳሹ እንደ ንፋጭ ሊሆን ይችላል ነገር ግን መጥፎ ጠረን ያለው፣ ቢጫ ወይም አረንጓዴ መሆን የለበትም። ይህ ከሆነ ግን የኢንፌክሽን ምልክት ነው። እናም ህክምና ማድረግ ይጠበቅባችኋል ማለት ነው።
📌 የጉንዮሽ ጉዳቶች
የጎንዮሽ ጉዳቶቹ ባደረጋችሁት የውርጃ አይነት ይወሰናል።
🔥የመድሃኒት ውርጃ ያለው የጎንዮሽ ጉዳቶች
➣ቁርጠት
➣ማቅለሽለሽ
➣ማስመለስ
➣ ተቅማጥ
➣ ትኩሳት
➣ ብርድ ብርድ ማለት
➣ራስ ምታት
➣ድካም
ትኩሳቱ በተጨማሪ የኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ስለሚችል ከትኩሳቱ ጋር ተያይዞ የሰውነት ህመም ፣ የደም መፍሰስ መጨመር ወይም የዳሌ ህመም ካጋጠማችሁ በአፋጣኝ ህክምና ማድረግ የሚኖርባችሁ ይሆናል።
🔥በህክምና ፅንስ ማስወረድ ያለው የጎንዮሽ ጉዳቶች
➣ ማቅለሽለሽ
➣ማስመለስ
➣ቁርጠት
➣ ድካም እና
➣ ማላብ ያሉ የጎንዮሽ ጉዳት የሚገጥማችሁ ይሆናል።
ሁለቱንም ውርጃ ካደረጋችሁ ወዲያው የንፅህና መጠበቂያ ፓድ ባትጠቀሙ ጥሩ ነው። ቢያንስ ከሁለት ሳምንት ቆይታ በኋላ እንድትጠቀሙ ይመከራል።
🔥 ፅንስ ከወረደ በኋላ የመጀመሪያ የወር አበባ እስከመቼ መምጣት አለበት ?
ፅንስ ማስወረድ የወር አበባ ዑደትን እንደገና እንዲጀምር ያደርገዋል። ከውርጃው በኋላ የወር አበባችሁ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መመለስ አለበት ። ማለትም የወር አበባችሁ ከውርጃው በኋላ ከ4 እስከ 6 ሳምንታት ውስጥ መመለስ አለበት።
ከውርጃ በኋላ የወር አበባ ወዲያው የመመለሱ እና ያለመመለሱ ነገር በፅንሱ እርዝማኔ ላይ የተመሰረተ ነው። ማለትም ከማስወረዳችሁ በፊት የምን ያህል ወራት እርጉዝ ነበራችሁ ማለት ነው። የእርግዝና ሆርሞኖቹ ከውርጃውም በኋላ ለጥቂት ሳምንታት ሊቆዩ ይችላሉ። ይህም መሆኑ የወር አበባ መዘግየትን ያስከትላል።
ከውርጃው በኋላ 4 ሳምንታት አሳልፋችሁ የወር አበባ ካላያችሁ የቤት ውስጥ የእርግዝና ምርመራ አድርጉ ወይም ሐኪም አማክሩ።ምክንያቱም ሂደቱ በትክክል ላይካሄድ ስለሚችል ነው።
የህክምናውን ውርጃ ካደረጋችሁ በኋላ የመጀመሪያው የወር አበባችሁ ከበፊቱ የወር አበባችሁ አንፃር ያነሰ ፍሰት ይኖረዋል ወይም ለአጭር ጊዜ ይፈሳችኋል። ይህም የሚሆነው በሆርሞኖች እና የወር አበባ ዑደት መመለስ ምክንያት ነው።
የመድሃኒት ውርጃ ካደረጋችሁ በኋላ የመጀመሪያው የወር አበባችሁ ከወትሮው የበለጠ ከባድ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም ሰውነታችሁ ሁሉንም ተጨማሪ ህዋሶች ከማህፀናችሁ ውስጥ ስላስወገደው ነው። እንዲሁም አንዳንድ ትንሽ የደም መርጋትም ሊፈሳችሁ ይችላል።
ከህክምናው ውርጃ በኋላ ያለው የመጀመሪያው የወር አበባ ቀላል ሊሆን ይችላል። በጥቂት ወራት ውስጥ ግን መስተካከል ይኖርበታል።
ነገር ግን ከውርጃ በኋላ የሚኖራችሁ ማንኛውም ፈሳሽ መጥፎ ሽታ ሊኖረው አይገባም። ማንኛውም መጥፎ ሽታ ያለው ፈሳሽ የኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል።
#እርግዝና
#health
#abortion
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: