ycliper

Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
Скачать

ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ክፍል 2 / Saint Moses the Black Part - 2

Автор: የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik

Загружено: 2019-01-02

Просмотров: 206927

Описание: በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን
​​ታላቁ አባት አቡነ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ተጋድሎአቸውን የፈጸሙት ግን በግብፅ ነው፡፡
መጀመሪያ ላይ እንደ አብርሃም በየዋህ ልቡና ሆነው ስነ ፍጥረትን በመመራመር
እግዚአብሔር አምላካቸውን ያገኙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ወላጆቻቸው ፀሐይ
ያመልኩ ስለነበር ከልጅነታቸው ጀምሮ ኃጢአት በሠሩ ቁጥር ‹‹ተው አምላካችን
ፀሐይ ይጣላሃል›› ይሏቸው ነበር፡፡ እሳቸው ግን ባደጉ ጊዜ ቀማኛ ዘራፊ ሆኑ፡፡
እየዘረፉ ብዙ ይመገቡ ስለነበር ከትልቅነታቸውና ኃይለኛነታቸው የተነሳ ‹‹በገ
ፈጅ›› እየተባሉም ይጠሩ ነበር፡፡
ብዙ ወርቅ ከባለ ሀብቶች ሰብስባ ለነዳያንና ለቤተክርስቲያን ልትሰጥ ትሄድ
የነበረችን አንዲት ክርስቲስቲያን ሴት ልጅ ሙሴና ግብረ አበሮቻቸው ለወርቁ
ሲሉ እርሷንም ማርከው ወሰዷት፡፡ ማታ ላይ ስለ ውበቷ ሲያወሩ እርሷ ግን
‹‹ስምህ ማን ነው?›› ስትላቸው ‹‹ሙሴ ነኝ›› ቢሏት ‹‹ይሄ ስምኮ እጅግ የተባረከ
ስም ነው….›› ብላ ስለ ሊቀ ነቢያት ሙሴና ስለ ክርስቶስ አስረዳቻቸው፡፡ ከዚህ
በኋላ በወላጆቻቸው ስለ ፀሐይ አምላክነት ሲነገራቸው ያደጉትን ነገር
መመርመር ጀመሩ፡፡ ‹‹ፀሐይ አምላክ ከሆነ እስከዛሬ ድረስ ሽፍታና ዘራፊ ሆኜ
ሰው ስገድልና ይህን ሁሉ ኃጢአት ስሠራ እንዴት ፀሐይ ሳታቃጥለኝ ቀረች?
ደግሞም ፀሐይ ጠዋት ወጥታ ማታ ትጠልቃለች ይህችስ እንዴት አስገኚ
ልትሆን ትችላለች ለራሷ አስገኚ አላት እንጂ…›› በማለት ፀሐይን፣ ጨረቃን፣
እሳትን፣ ነፋስን በየተራ አምላክ መሆናቸውን አለመሆናቸውን በሚገባ ከፈተኑና
ከመረመሩ በኋላ ‹‹የፀሐይ የጨረቃ የሁሉ አስገኚ አምላክ ተናገረኝ›› ብለው
ሲጸልዩ ከሰማይ ድምፅ መጥቶላቸው ወደ ገዳም ሄደው ከአባቶች ትምህርተ
ሃይማኖትን እንዲማሩ ተነገራቸውና ወደ አስቄጥስ ገዳም ሄደው መምህር
ኤስድሮስ ሁሉንም ነገር አስተምረው ለማዕረገ ምንኩስና አበቋቸው፡፡
መጀመሪያ ወደ ገዳሙ ሲሄዱም ይዘርፉበትና ይቀሙበት የነበረውን ስለታም
መሣርያ እንደያዙ ስለነበር ያዩአቸው መነኮሳት ሁሉ ‹‹ሊገድለን መጣ›› ነበር
ያሉት፡፡ ከዚህም በኋላ ለመነኮሳቱ ሁሉ የሚላላኩ ሆኑ፡፡ ትንሹም ትልቁም ‹‹ሙሴ
ይህን አድርግልኝ›› ይሉታል እርሱም ሁሉንም እሺ ይላል፡፡ ራሱን በትሕትና ዝቅ
በማድረግ በተጋድሎ እየኖረ ተአምራትን ማድረግ ጀመረ፡፡ በጸሎቱ ዝናብ ያዘንብ
ነበር፤ ለቅድስና ደረጃ ከበቁም በኋላ 40 ዓመት ሙሉ ከሰው ሳይገናኙ ብቻቸውን
ዘግተው ከኖሩ በኋላ ለ500 መነኮሳት አበምኔት ሆነው ተሾሙ፡፡ ቀን ወንጌል
ሲያስተምሩ ይውሉና ሌሊት እየተነሱ ከበረሃ ሄደው ለሁሉም መነኮሳት ውኃ
ይቀዱላቸው ነበር፡፡ አገልግሎታቸው የታይታ እንዳይሆንባቸው አረጋውያን
መነኮሳት መተኛታቸውን ካረጋገጡ በኋላ የግብፅ በረሃን አቋርጠው ከሩቅ ሥፍራ
ሄደው ውኃ እየቀዱ መነኮሳቱ ሳያዩአቸው በየደጃፋቸው ላይ ያስቀምጡላቸው
ነበር፡፡
ብዙ መነኮሳትም ወደ አቡነ ሙሴ እየመጡ የሕይወትን ትምህርት ይማሩ ነበር፡፡
በአንድ ወቅት አንድ ወንድም አባ ሙሴን ‹‹አንድን አገልጋይ ባጠፋው ጥፋት
የተነሣ ጌታው መታው፡፡ አገልጋዩ ምን ማለት አለበት?›› ብሎ ጠየቃቸው፡፡ አባ
ሙሴም ‹‹አገልጋዩ ብፁዕ ከሆነ፣ አጥፍቻለሁና ይቅር በለኝ ማለት አለበት››
አሉት፡፡ ‹‹ሌላ አይጠበቅበትምን?›› ሲል ያ ወንድም ጠየቃቸው፡፡
‹‹አይጠበቅበትም፣ ለጊዜው ለጥፋቱ ኃላፊነቱን ወስዶ አጥፍቻለሁ ካለ ጌታው
ይቅር ይለዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ዓለማው በባልንጀራ ላይ ላለመፍረድ ነው፡፡ በእውነቱ
ጌታችን የግብፅን በኩራት ሁሉ ሲመታ ሰው ያልሞተበት አንድም ቤት
አልነበረም›› ብለው መለሱለት፡፡ ያም ወንድም ‹‹ምን ማለት ነው?›› አላቸው፡፡
እሳቸውም ‹‹ሁላችንም የየራሳችንን ጥፋቶች ካየን የባልንጀራችንን ለማየት ዕድል
አንሰጥም፡፡ በራሱ ቤት ሰው የሞተበት በጐረቤቱ ልቅሶ ለማልቀስ አይሄድም፡፡
ለባልንጀራ መሞት ማለት ለራስ ጥፋት ትኩረት በመስጠት፣ የሌላውን ጥፋት
ከቁም ነገር አለመቁጠር ነው፡፡ ማንንም አትጉዳ፣ በማንም ላይ ክፉ አታስብ፣
ክፉ የሚሠራውን ሰው አትናቀው፣ በባልንጀራው ላይ ክፉ በሚሠራ ሰው ላይ
አትተማመን፣ በባልንጀራው ላይ ክፉ ከሚሠራ ሰው ጋር አትደሰት፣ ለባልንጀራ
መዋቲ መሆን ማለት ይህ ነው፡፡ በማንም ላይ አትማረር፣ ነገር ግን ሁሉንም
እግዚአብሔር ያውቃል በል፡፡ ከሚያማ ሰው ጋር አትተባበር፣ በሐሜቱም
አትደሰት፣ ወንድሙን የሚያማውን ሰውም አትጸየፈው፡፡ አትፍረድ ማለት ትርጉሙ
ይህ ነው፡፡ በማንም ላይ የጥላቻ ሀሳብ አይኑርህ፣ ጥላቻ ልብህን
እንዲያሸንፈውም አትፍቀድለት፡፡ ባልንጀራውን የሚጠላውን አትጥላው፣ ሰላም
ማግኘት ማለት ይህ ነው…›› ብለው መከሩት፡፡
በዕድሜአቸው መጨረሻ አካባቢ ቡራኬ ለመቀበል ከመነኮሳት ደቀ
መዛሙርቶቻቸው ጋር ወደ አባ መቃርስ ሄዱ፡፡ አባ መቃርስም ‹‹ልጆቼ ከናንተ
መካከል በሰማዕትነት የሚሞት›› አለ ብለው ትንቢት ሲናገሩ ሙሴ ጸሊምም
‹‹አባቴ ያ ሰው እኔ ነኝ፣ ‹ሰይፍ የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ› የሚል ቃል አለ፡፡
ይህን ጊዜ በጉጉት ስጠባበቀው ነበር›› አላቸው፡፡ እንደተባለውም የበርበር ሰዎች
ገዳሙን ዘርፈው መነኮሳቱን ሊገድሉ ሲመጡ ደቀመዛሙርቶቻቸው ‹‹ሸሽተን
እናምልጥ›› ሲሏቸው አቡነ ሙሴ ግን ‹‹በጎልማሳነቴ ጊዜ ደም አፍስሼያለሁና
አሁን የእኔም ደም ሊፈስ ይገባል›› በማለት ራሳቸውን ለመሰየፍ አዘጋጅተው
ጠበቋቸውና በርበሮች ሰኔ 24 ቀን አንገታቸውን በሰይፍ ቆርጠዋቸዋል፡፡
ፈርተውና ሸሽተው የነበሩት ደቀመዛሙርቶቻቸውም ተመልሰው አብረዋቸው
ተሰይፈዋል፡፡
የአባታችን የሙሴ ጸሊም ቅዱስ ሥጋቸው በገዳመ አስቄጥስ በክብር ይገኛል፡፡
ግብፆች አቡነ ሙሴ ጸሊምን በእጅጉ ያከብሯቸዋል፡፡ በስማቸው ጽላት ቀርጸው
ቤተክርስቲያን ሠርተው ሥዕላቸውን አሠርተው ገድላቸውን ጽፈው
በስንክሳራቸው መዝግበው የዕረፍታቸውን መታሰቢያ በደማቅ ሁኔታ ነው
የሚያከብሩት፡፡ የአቡነ ሙሴ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው
ይማረን፡፡ ኣሜን

Не удается загрузить Youtube-плеер. Проверьте блокировку Youtube в вашей сети.
Повторяем попытку...
ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ክፍል 2 / Saint Moses the Black Part - 2

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио

Похожие видео

አባ ገብረ ክርስቶስ - ክፍል 1 / Aba Gebre Kirstos - Part 1  Abdel Messih el Habashi

አባ ገብረ ክርስቶስ - ክፍል 1 / Aba Gebre Kirstos - Part 1 Abdel Messih el Habashi

ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ክፍል 1 / Saint Moses the Black Part - 1

ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ክፍል 1 / Saint Moses the Black Part - 1

ሳምሶን: በፍቅር የወደቀው ጠንካራ ሰው: ከሳምሶን ጥንካሬ በስተጀርባ ያለው እውነት እና የሳምሶን ሙሉ ታሪክ

ሳምሶን: በፍቅር የወደቀው ጠንካራ ሰው: ከሳምሶን ጥንካሬ በስተጀርባ ያለው እውነት እና የሳምሶን ሙሉ ታሪክ

Соломон и царица Савская . Худ.фильм ( не исламское производство )

Соломон и царица Савская . Худ.фильм ( не исламское производство )

እግዚአብሔር ሲጠራው ሁሉንም ነገር ትቶ ሄደ || የአብርሃም ጥሪ (የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ)

እግዚአብሔር ሲጠራው ሁሉንም ነገር ትቶ ሄደ || የአብርሃም ጥሪ (የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ)

አስደናቂው የነብዩ ሙሴ ታሪክ// The amazing story of prophet Moses

አስደናቂው የነብዩ ሙሴ ታሪክ// The amazing story of prophet Moses

Yarbegnaw Lij Full Amharic Movie on ebs cinema  | ebs | ebs cinema | seifu on ebs

Yarbegnaw Lij Full Amharic Movie on ebs cinema | ebs | ebs cinema | seifu on ebs

ቅዱስ አባ ጳውሊ ወ አባ እንጦንስ | Antony the Great and St Paul the first Hermit

ቅዱስ አባ ጳውሊ ወ አባ እንጦንስ | Antony the Great and St Paul the first Hermit

ታላቁ ነብይ ኤልያስ  - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች 20 -  መንፈሳዊ ፊልም በአማርኛ - @meba-tv - Eotc tv - ስንክሳር

ታላቁ ነብይ ኤልያስ - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች 20 - መንፈሳዊ ፊልም በአማርኛ - @meba-tv - Eotc tv - ስንክሳር

ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 1 / Saint Simon - Part 1

ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 1 / Saint Simon - Part 1

የሞዓባውያን ሚስጥራዊ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) @Meba_tv

የሞዓባውያን ሚስጥራዊ ታሪክ - መባዕ ቲቪ (Meba TV) @Meba_tv

የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ፊልም / ye sematu qdus estifanos film

የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ፊልም / ye sematu qdus estifanos film

[ክፍል-1] የታላቁ ሊቅ ቅድስ ዮሐንስ ታሪክ መንፈሳዊ ፊልም - Ethiopian Orthodox

[ክፍል-1] የታላቁ ሊቅ ቅድስ ዮሐንስ ታሪክ መንፈሳዊ ፊልም - Ethiopian Orthodox

Фильм Мухаммад Посланник Всевышнего с.а.в. на русском языке HD КАЧЕСТВО

Фильм Мухаммад Посланник Всевышнего с.а.в. на русском языке HD КАЧЕСТВО

የጌታ ወዳጅ አባ ቢሾይ / Aba Bishoy

የጌታ ወዳጅ አባ ቢሾይ / Aba Bishoy

የበገና መዝሙር ሙሉ አልበም ዲ/ን አቤል ተስፋዬ

የበገና መዝሙር ሙሉ አልበም ዲ/ን አቤል ተስፋዬ

እንደ ኢዮብ ታጋሽ-መጽሐፈ ኢዮብ(ምዕራፍ 1-42) መጽሐፍ ቅዱስ ትረካ : ሙሉ መንፈሳዊ ታሪክ በአማርኛ

እንደ ኢዮብ ታጋሽ-መጽሐፈ ኢዮብ(ምዕራፍ 1-42) መጽሐፍ ቅዱስ ትረካ : ሙሉ መንፈሳዊ ታሪክ በአማርኛ

ዝምተኛው መነኩሴ አባ ዮስጦስ - ክፍል 1 / Aba Yostos - Part 1 Orthodox Tewahedo Film - Ye Kidusan Tarik

ዝምተኛው መነኩሴ አባ ዮስጦስ - ክፍል 1 / Aba Yostos - Part 1 Orthodox Tewahedo Film - Ye Kidusan Tarik

Moses (1995)

Moses (1995)

ቅዱስ ሙሴ ፀሊም መንፈሳዊ ፊልም || saint moses black spritual full orthodox movie

ቅዱስ ሙሴ ፀሊም መንፈሳዊ ፊልም || saint moses black spritual full orthodox movie

© 2025 ycliper. Все права защищены.

  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности

Контакты для правообладателей: [email protected]