🔴 አዲስ የሆሳዕና ዝማሬ "ሆሳዕና" ሊቀ ዲያቆናት ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ | Deacon Zemari Kedametsega Official
Автор: Kedametsega Yohanis Official - ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
Загружено: 2023-04-07
Просмотров: 133943
Описание:
ሆሳዕና ሆሳዕና ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት
ህፃናቱ ሁሉ ድንጋዮች ሳይቀሩ ለዘመሩለት
ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት
አዝ
በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ
የተባረከ ነው ቅዱስ ነው መንፈሱ
ሰላምን የሚሰብክ የሚናገር ፍቅርን
በአህያ ውርንጫ መጥቷል ንጉሳችን
አዝ
ዘንባባውን ይዘን ህፃን አዛውንቱ
ልብሳቸውን ሳይቀር አንጥፈው በፉቱ
ሆሳዕና ብለው ዘመሩ በልዕልታ
ግባ ንጉሳችን የሠራዊት ጌታ
አዝ
ዘመን ለሰጠንን እንዘምርለት
የምስጋናን መስዋዕት በፊቱ እንሰዋለት
እንኳን እኛን ቀርቶ ድንጋይ ያናግራል
ከሚጠቡ አንደበት ምስጋናን ይወስዳል
አዝ
እኛ ለክርስቶስ እናስፈልጋለን
ቅዱሳኑን ልኮ መፈታትን ይስጠን
በትህትና ወድቀን በልባችን ይግባ
እንደህፃናቱ እንያዝ ዘንባባ
አዝ
መድሃኒት ለሰው ልጅ ስለተገለጠ
የመርገም ጨርቃችን ስለተወጠ
ሰላም በሰማያት ሆነ በምድር
ክብር እና ምስጋና ለእርሱ ለእግዚአብሔር
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: