ጥር 22 | ቅዱስ ዑራኤል | ለምን ይከብራል? || Tir 22 | kidus Urael
Автор: Betemariam
Загружено: 2026-01-29
Просмотров: 11358
Описание:
#ጥር_21 #ቅዱስ_ዑራኤል #ዑራኤል #Kidus_Urael
እንኳን ለሊቀ መላእኩ ቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ጥር 22 ቀን በሰላም በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ !!!
በዚች ዕለት ቅዱስ ዑራኤል በዓለ ሢመቱ የሚከበርበት ዕለት ሲሆን በቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡
ቅዱስ ዑራኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት መካከል አንዱ መላዕክ ሲሆን፤ ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው፡፡ በመሆኑም መጽሐፈ ሄኖክ እንደሚገልጸው መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል፡፡ ምሥጢረ ሰማይንና ሰማያዊውን ዕውቀት ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራው ይኸው ገናና መልአክ ነው፡፡ (መጽሐፈ ሄኖክ 28፥13)
"የፍጥረቱ ሁሉ ገዥ ጌታ በሰማይ ሠራዊት የሾመው መላእኩ ዑራኤልም በኔ እውቀትን አሳደረብኝ፡፡
መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በዓመት ሦስት ዐበይት በዓላት አሉት፡፡
ጥር ፳፪ በዓለ ሲመቱ፤
መጋቢት ፳፯ የጌታችንን ክቡር የሆነ ወርቀ ደሙን ለዓለም የረጨበት፤
ሐምሌ ፳፪ ቀን ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ነው፡፡
የሊቀ መላእክት የቅዱስ ዑራኤል ረድኤት በረከት ይደርብን፡፡ አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: