ደረጀ ሙላቱ// Dereje Mulatu- (ኤሎሄ//Elohe)
Автор: Dereje Mulatu Official
Загружено: 2019-12-06
Просмотров: 370034
Описание:
እኔኑ ፍለጋ አመጸኛውን ሰው
ተዋረድክ ኢየሱስ ክብር እንደሌለው
እኔን ግን ከውርደት ከማጥ አወጣኸኝ
ተመስገን በለረፋት በጣር የወለድከኝ
ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ
እስክትል የተሰቃየህ
ስለኔ ከሞት ልታድነኝ
የበዛ የመስቀል ጣርህ
ስለኔ ለከፈልከው ዋጋ
መታሰቢያ ላድርግ እስኪ ዛሬ
ምሰጥህ ምንም ባይኖረኝም
ላክብርህ በፊትህ ዘምሬ
ማንም ይወድህ ዘንድ ደም ግባት የለህ
የህማም ሰው ነበርክ ደዌ ያደቀቀህ
በመገረፍ ቁስልህ እኔ ተፈወስኩኝ
ተመስገን በሞትህ ከሲኦል አመለጥኩኝ
በመከራ ሰአት በዛ ጭንቀትህ
አብ አባትህ እንኳን ዝም አለ ተወህ
የሁላችን በደል በላይህ ላይ ሆነ
ተመስገን እንዳንተ የለም የታመነ
ልታዘዝህ ዛሬ ደስ ላሰኝህ
ልብህ እንዳያዝን ተረስቶኝ ቃልህ
ዋጋ ከፍለህልኝ ሰው አድርኸኛል
ክበር የእኔ ጌታ ደምህ ፈሶልኛል
Повторяем попытку...
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео
-
Информация по загрузке: