ycliper

Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
Скачать

#ደብረ

Автор: Fere Tebebat Tube ፍሬ ጥበባት ቲዩብ

Загружено: 2025-08-21

Просмотров: 197

Описание: #ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚኣከ ይትፌስሑ(መዝ.88÷12)               
በዚህ ርዕስ ሥር
1. በዓሉ የሚከበርበትን ምክንያት/
ከሐዋርያት ሦስቱ ሐዋርያት ብቻ መመረጣቸው ፤ ከነቢያት ሙሴና ኤልያስ መገለጣቸው ስለምን ነው?
2. ደብረታቦር የተመረጠበት ምክንያትና ምሳሌነቱ
3. የበዓሉ መጠሪያ ስሞች (ደብረ ታቦር / ቡሄ/ ቡሔ መባሉ ስለምንድ ነው?)
4. ችቦ የመብራቱ ፣ ሙልሙል ዳቦ የመጋገሩና የጅራፍ ማጮኽ ምክንያት እንመለከታለን፡፡

✔ 1. ይህ በዓል ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን የሚከበረው ጌታችን የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅነቱን ያስመሰከረበት፣ ጌትነቱን እና ክብሩን የገለጠበት በመሆኑ ነው፡፡ (ማቴ.17÷1 ማር.9÷2 ሉቃ.9÷28 2ጴጥ.1÷16-18)፡፡

👉 ጌታችን ሐዋርያትን ‹‹ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ብለው ይሉታል? ›› ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ቅድስናህን ዓይተው ሙሴ ነህ ይሉሃል፤ የኃይል ሥራህን ድንግልናውንም ዓይተው ኤልያስ ነህ የሚሉህ አሉ ……… ብለውት ነበረና እግዚኣ ሙሴ ወኤልያስ (የነቢያት ጌታ) መሆንኑን ለመግለጥ፤ አንድም ጌታችንም መልሶ ‹‹ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ? ›› አላቸው ቅዱስ ጴጥሮስም እስከ ክርቶስ ተብሎ የተነገረልህ ‹‹ አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ ›› አለው (ማቴ.16÷13-20/ ትን.ዳን.9÷25) ይህን በፍጡር አንደበት የተመሰከረውን ጌትነቱን በአብ ምስክርነት ለማጽናት እና በተግባር ለመግለጥ የሐዋርያትንም እምነታቸውን ለማጽናት አዕማደ ሐዋርያት የሆኑትን ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ ያዕቆብ፣ ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ ወደ ቅዱሱ ተራራ አወጣቸው፡፡

👉 ስለምን እነዚህን ብቻ አወጣቸው ቢሉ ለፍቅሩ ይሳሳሉና በፍቅሩ ይናደዳሉና ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ እሞታለሁ ቢለው " አንተስ አትሞትም እኔ እሞታለሁ እንጂ " ማለቱ እኒም እኔ የምጠጣውን ጽዋ (ሞት) ልትጠጡ ትችላላችሁን? ቢላቸው " አዎ እንችላለን " (ስለ አንተ እንሞታለን) ማለታቸው እጅግ ቢወዱት ነው ስለዚህ ሦስቱን መረጣቸው፡፡

👉 ቀሪዎችን ሐዋርያትን ከእግረ ደብር አቆይቷቸዋል

👉 መልኩም በፊታቸው ተለወጠ፤ ፊቱም ከፀሓይ ይልቅ አበራ፤ ልብሱም ልብስ አጣቢ ከሚያነጻው ይልቅ እንደ በረድ ፀዓዳ ሆነ፡፡ ‹‹ እነሆ ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው›› ቅዱስ ጴጥሮስም ጌታን ‹‹ አቤቱ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ ሦስት ቤቶችን በዚህ እንሥራ፤ አንዱን ለአንተ÷ አንዱንም ለሙሴ÷ አንዱንም ለኤልያስ አለው›› በዚህ ቃል የትህትና እና የደካማነት ምልክት አለበት፡፡ ትህትና ያልነው ቅዱስ ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው ራሱንና ባልንጀሮቹን እንደ ባሮች፤ ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች (የጌታ ባለማሎች) አድርጎ አስቧልና፡፡ ደካማነት የተባለው ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን (ሰው የሆነበት) ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና
ራሱን የሚሰውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው፡፡ ስለዚህም ጌታችን ምድራዊ ቤት እንደማያስፈልገው ያስረዳው ዘንድ የክብሩ መገለጫ የሆነ ብሩህ ደመና መጥቶ እንደቤት ሁኖ ጋረዳቸው፡፡ ‹‹እነሆ በደመናው ውስጥም የምወደው በእርሱም ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል ቃል
መጣ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው ደንግጠው በግንባራቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸው ተነሡ አትፍሩም አላቸው፡፡ ዓይናቸውንም አቅንተው ዓዩ ነገር ግን ከጌታችን ከኢየሱስ ብቻ በቀር ያዩት ማንም አልነበረም፡፡ ››

👉 ከነቢያት ሁሉ ለይቶ ሙሴና ኤልያስ እንዲገለጡ ማድረጉ ስለምንድን ነው ቢሉ ሙሴ ከአምላክ ጋር 570 ጊዜ ያህል ቃል ለቃል ተነጋግሮት ነበርና ባለማልነቴ ይገለጥ ዘንድ ባይህ እወዳለው አለው፡፡ አምላክም ፊቴን ዓይቶ አንድ ሰዓት ስንኳ መቆም የሚቻለው የለም ብሎ መለሰለት ሙሴም ይህ ካልሆነማ ባለሟልህ መባሌ ምኑ ላይ ነው በቃልማ ሌሎቹንስ ታናግር የለምን ቢለው አምላክም " ድኅረሰ ትሬኢ ገጽየ " መሥዋዕት ሁኜ በምቀርብበት ጊዜ (በዘመነ ሥጋዌ) እታይሃለሁ ብሎት ነበርና ይህ እንዲፈጸም፡፡ (ዘጸ.33÷18-23)፤ ኤልያስ ስለአምላክ እጅግ በመቅናቱ ተስፋ ተሰጥቶት ነበርና፡፡ ክብሩ በተገለጠ ጊዜ ግን ሙሴ ‹‹ትኄይሰኒ መቃብርየ›› (መቃብሬ ትሻለኛለች ብሏል)፤ ኤልያስም ወደ እሳት ሠረገላው ተመልሷል፡፡
• አንድም፡- ሙሴ ኤልያስ ይሉሃል ብለውት ነበረና እግዚኣ ሙሴ ወኤልያስ መሆኑን በራሳቸው አንደበት ለማስመስከር፡፡
• አንድም፡- የሕያዋን (ሞት ያላገኛቸው) የሙታን (ሞት ያገኛቸው) አምላክ መሆኑ ለማጠየቅ ነው ከእርሱ በቀር
የሙሴን መቃብር (ይሁ.ቍጥ.9)፤ ኤልያስም የተሰወረባት (ብሔረ ሕያዋንን) የሚያውቅ የለምና፡፡
• ፍጻሜው ግን፡- ደብረ ታቦር የቤተክርስቲያንና የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ እንድትሆን ነው፡፡

✔ 2. ደብረታቦር የተመረጠበት ምክንያትና ምሳሌነቱ፡-
• ደብረ ታቦር ማለት ደብር ተራራ ሲሆን ታቦር የቦታው ስም ነው ከኢያቦር ወገን የነበረ ቦር የሚባል ሰው ነበረና በሱ ስም ታቦር አሉት "ቦር" ማለት ትልቅ ማለት ሲሆን "ታ" ን ጨምረው ታቦር ብለውታል።

👉 በደብረ ታቦር ያደረገው በሌላ ያላደረገው ስለም ነው ቢሉ ትንቢቱ ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ትንቢቱ ‹‹ ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ›› (መዝ 88÷12) ያለው ነው። ምነው ክብሩን የገለጠ በታቦር አይደለምን አርሞንዔምንም አነሳ ቢሉ ብርሃኑ እስከ አርሞንዔም ደርሷልና ነው፡፡
ምሳሌው ፡- በዚህ ተራራ ላይ ነቢያቱ ዲቦራ ከባርቅ ጋር በመሆን የከነዓናውያን ንጉሥና የጦር መሪ ሲሳራንና ኢያቡስን በጦርነት ድል አድርገውበታል (መሳፍንት 4፥5–24) ጌታም በልበ ሐዋርያት ያደረ ሰይጣንን ድል ነሥቶበታልና፡፡
• ደብረ ታቦር የቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ብሉይን የሚወክሉ ነቢያት፤ ሐዲስንም የሚወክሉ ሐዋርያት እንዲሁም ሐጋጌ ሕግ የሆነም ጌታ እንደተገኙ በእግዚአብሔር ቤትም ብሉይና ሓዲስ እንደሚነገሩ ምእመናንም በእነዚህ ሕግ እንደሚመሩ ያስረዳል፡፡ መምህር ጳውሎስም ስለዚህ ነገር ሲያስረዳ ‹‹በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋልና፤ የሕንጻው የማዕዘን ራስ ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ እርሱም ሕንጻ ሁሉ የሚያያዝበት÷ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግንብ የሚያድግበት ነው፡፡ እናነተ በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ልትሆኑ በእርሱ ታነጻችሁ፡፡›› አለ፡፡ (ኤፌ.2÷20-21)
• አንድም፡- የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ናት ነቢያትም ሐዋርያት አንድ ሁነው እንዲወርሷት፤ ከመዓስባን ሙሴን
ከደናግላን ኤልያስን አመጣ መዓስባንና ደናግላን አንድ ሁነው እንደሚወርሷት፤ ከምዉታን ሙሴን ከሕያዋን ኤልያስ አመጣ ሁሉም በትንሣኤ እንደሚወርሷት ለማጠየቅ፡፡

✔ 3. የበዓሉ መጠሪያ ስሞች (ደብረ ታቦር / ቡሄ/ ቡሔ መባሉ ስለምንድ ነው?)

👉 ደብረ ታቦር የተባለው ጌታ ክብሩን የገለጠበት ስፍራ ደብረ ታቦር ስለሆነ በዚሁ በዓሉ ስያሜውን አግኝቷል፡፡

👉 ቡሔ ይባላል ፡- ቡሄ ብርሃን ማለት ነው በደብረታቦር ቧ ብሎ የተገለጠውን የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል፤ የልብሱንም እንደ ነጭ በረዶ ጸዓዳ መሆን ያስረዳል፡፡
• አንድም፡- ቡሔ ማለት መላጣ (ገላጣ) ማለት ነው፡፡
ይኸውም በበዓሉ ዋዜማ ልጆች ‹‹ ቡሔ በሉ፤ ቡሔ መጣ ፣ ያ መላጣ፣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ›› ይላሉ እዚህ ላይ ቡሄ ያለው ዳቦውን ነው፡፡
• አንድም፡- ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንደሚባል ወቅቱ በሃገራችን የጸዓተ ክረምት ዋዜማ ስለሆነ የክረምቱ አፈናው ተወግዶ /ተጋምሶ/ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት ፤ በዶፉና በጎርፉ ተሸፍና የነበረች መሬት የምትገለጥበት በመሆኑ ነው፡፡
• አንድም፡- ቡሔ (ቡሔእየ) ተብሎ ይተረጎማል ይኸውም የደብረታቦር እለት እርሾ ሳይገባበት ተቦክቶ የሚጋገረውን
ኅብስት ያሳያል፡፡

✔ 4. ችቦ የመብራቱ ፣ የሙልሙል ዳቦ የመጋገሩና የጅራፍ ማጮኽ ምክንያት፡-

👉 መብራት የሚበራው 12 ለ13 ዋዜማ ሌሊት በ3 ሰዓት ነው ።
• የጌታችን ክብሩ በተገለጠበት ጊዜ ብርሃኑ የሌሊቱን ጨለማ ገፍቶት እስከ አርሞንዔም ደርሶ ነበርና በዚያ አካባቢ የነበሩ እረኞች በሁኔታው ተገርመው ቀንም መስሎአቸው ሌሊቱም ተዘንግቷቸው በዚያው ቆይተው ነበርና ቤተሰዎቻቸው ምን አግኝቷቸው ይሆን በማለት መብራት አብርተው (ችቦ ይዘው)፣ የሚመገቡትን ይዘው ወገኖቻቸውን ፍለጋ ወጥተዋል እረኞችም ያሉበትን ቦታ ለቤተሰዎቻቸው ጅራፍን በማጮኸ አመልክተዋቸዋልና ይህን ለማሰብ ነው፡፡
• ዋናው ምሥጢሩ ግን፡- የችቦው ብርሃን የጌታ ክብር መገለጡን፣ የጅራፋ ጩኸት ሐዋርያትን ያስደነገጣቸው የአብ የምስክርነቱ ቃል ምሳሌ ሲሆን፣ ኅብስቱ ጌታችን በመስቀል ላይ መሥዋዕት የመሆኑ (የሥጋ ወደሙ) ምሳሌ ነው፡፡
• ማስታወሻ፡- ከላይ እናዳየነው ጅራፋ መጮኹ የአብ የምስክርነቱ ቃል ምሳሌ ነው ይኸውም በታቦር ተራራ ላይ እንደሆነም ተገልጧል ስለዚህ ዛሬም ምሳሌነቱን ለማጉላት ጅራፍ የማጮኹን ሥርዓት በተራራ ማድረግ የተሻለ ነው፡፡ ይቆየን

ዲ/ን አየለ ኮኮቤ
‪@Arsi_Chole.Zemarian21‬

Не удается загрузить Youtube-плеер. Проверьте блокировку Youtube в вашей сети.
Повторяем попытку...
#ደብረ

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио

Похожие видео

🔴እኛስ ሀገራችን በ5ቱ ዘማሪያን Egnas Hagerachin   /@AbelBirhanu

🔴እኛስ ሀገራችን በ5ቱ ዘማሪያን Egnas Hagerachin /@AbelBirhanu

Срочные переговоры с Путиным / Вывод части войск

Срочные переговоры с Путиным / Вывод части войск

አርሲ ጮሌ የገንቦ @ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን  አመሰራረትና አሁን ከአባቶች አንደበት Arsi chole Genbo @Saint Michael @History

አርሲ ጮሌ የገንቦ @ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አመሰራረትና አሁን ከአባቶች አንደበት Arsi chole Genbo @Saint Michael @History

🔴አንዲት በግ ፍለጋ በዘማሪት ዶ/ር ስምረት መኩሪያ አዲስ ዝማሬ የተሻለ ነገር አስበህልኝ ነው || በዘማሪት እድላዊት ፍሬው @EOTCTV@AbelBirhanu

🔴አንዲት በግ ፍለጋ በዘማሪት ዶ/ር ስምረት መኩሪያ አዲስ ዝማሬ የተሻለ ነገር አስበህልኝ ነው || በዘማሪት እድላዊት ፍሬው @EOTCTV@AbelBirhanu

ማርያም አርጋለች   የዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ዝማሬ ፤ በግንቦት አንድ ሚዲያ ዘማሪያን #newethiopianmezmur @abelbirhanu1 @-mahtot

ማርያም አርጋለች የዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ዝማሬ ፤ በግንቦት አንድ ሚዲያ ዘማሪያን #newethiopianmezmur @abelbirhanu1 @-mahtot

Look it's our community custom

Look it's our community custom

live አስቸኳይ መልእክት ከጥምቀት በዓል በፊት ይስሙት /ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም

live አስቸኳይ መልእክት ከጥምቀት በዓል በፊት ይስሙት /ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም

Про посещения ложного Иисуса

Про посещения ложного Иисуса

እርሱ ጌታ የሆነ ተወልዶላችዋል በመ/ር እንደሻው ገዛኽኝ @Arsi_Chole.Zemarian21

እርሱ ጌታ የሆነ ተወልዶላችዋል በመ/ር እንደሻው ገዛኽኝ @Arsi_Chole.Zemarian21

ሰራተኛዋ አደይ ክፍል 180 ll WEG Tube || ወግ ቲዩብ

ሰራተኛዋ አደይ ክፍል 180 ll WEG Tube || ወግ ቲዩብ

Почему СТАРЦЫ БОЯЛИСЬ СВЯТОК больше, чем других дней

Почему СТАРЦЫ БОЯЛИСЬ СВЯТОК больше, чем других дней

🔴ኑ አርሲ ጮሌ ቦጂ ቅ/እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያንን በ2.2ሚሊየን ብር ቦታ ገዝተን እናስፋ   Boji Kidus Egziabher Ab Church

🔴ኑ አርሲ ጮሌ ቦጂ ቅ/እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያንን በ2.2ሚሊየን ብር ቦታ ገዝተን እናስፋ Boji Kidus Egziabher Ab Church

🔴 LIVE | ቀጥታ ከ4 ኪሎ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ የዋዜው ማህሌት ደምቋል | ጥር 6, 2018 ዓ.ም |Mahlet at 4 Kilo Holy Trinity

🔴 LIVE | ቀጥታ ከ4 ኪሎ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ የዋዜው ማህሌት ደምቋል | ጥር 6, 2018 ዓ.ም |Mahlet at 4 Kilo Holy Trinity

January 2, 2026

January 2, 2026

ቃና ዘገሊላ በአርሲ ጮሌ ክፍል አንድ Zagalila part @one @Arsi @chole  @fenot2721 @Arsi_Chole.Zemarian21

ቃና ዘገሊላ በአርሲ ጮሌ ክፍል አንድ Zagalila part @one @Arsi @chole @fenot2721 @Arsi_Chole.Zemarian21

🔴 Demena Honesh ደመና ሆነሽ በዘማሪ ዲ/ን ደመቀ/ለይኩን/ ብርሃን

🔴 Demena Honesh ደመና ሆነሽ በዘማሪ ዲ/ን ደመቀ/ለይኩን/ ብርሃን

🔴 ጥሪ 7 | አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ | ንምንታይ ነኽብሮ ? #ቅድስት_ሥላሴ#tigrignamezmur #sibket #theotokos #ስብከት

🔴 ጥሪ 7 | አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ | ንምንታይ ነኽብሮ ? #ቅድስት_ሥላሴ#tigrignamezmur #sibket #theotokos #ስብከት

የገና (የልደት) መዝሙራት ስብስብ//Christmas Mezmur Collection #እሰይ ተወለደ #በኤፍራታ ምድር... @መቅደስዘኦርቶዶክስሚዲያ

የገና (የልደት) መዝሙራት ስብስብ//Christmas Mezmur Collection #እሰይ ተወለደ #በኤፍራታ ምድር... @መቅደስዘኦርቶዶክስሚዲያ

Te`amira Fikirki Mariyam በጮሌ ደ/ገ/ቅ/ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች የማኅሌተ ጽጌ ወረብ

Te`amira Fikirki Mariyam በጮሌ ደ/ገ/ቅ/ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች የማኅሌተ ጽጌ ወረብ

Ba`ed Amliko ባዕድ አምልኮ @Arsi_Chole.Zemarian21

Ba`ed Amliko ባዕድ አምልኮ @Arsi_Chole.Zemarian21

© 2025 ycliper. Все права защищены.



  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности



Контакты для правообладателей: [email protected]